1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሥራኤልና የአፍሪቃ ግንኙነት፤

ሐሙስ፣ ሰኔ 5 2006

የአሥራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን እ ጎ አ ከ 2009 ወዲህ እንደገና 5 የአፍሪቃን አገሮች ለ 10 ቀናት ለመጎብኘት በዚህ ሳምንት ተንቀሳቅሰዋል። የሚጎበኟቸው አገሮች፤ ሩዋንዳ ፤ አይቮሪኮስት፤ ጋና ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው።

https://p.dw.com/p/1CHWu
ምስል Reuters

የአሥራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን እ ጎ አ ከ 2009 ወዲህ እንደገና 5 የአፍሪቃን አገሮች ለ 10 ቀናት ለመጎብኘት በዚህ ሳምንት ተንቀሳቅሰዋል። የሚጎበኟቸው አገሮች፤ ሩዋንዳ ፤ አይቮሪኮስት፤ ጋና ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው።

Infografik Karte Verbreitung von Mobilfunkverträgen in Afrika mit Ländernamen ENG

ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፣ «ከአፍሪቃ ጋር ያለ ግንኙነት ፣ ሥልታዊ ጠቀሜታን የሚያስቀድም፤ ለፀጥታ፤ ፖለቲካና የኤኮኖሚ ጥቅም ቅድሚያ የሰጠ ነው» ሲሉ ተናግረዋል። ስለውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ጉብኝት ፣ ባአጠቃላይ ስለ እሥራኤልና አፍሪቃ ግንኙነት ፣ የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ ፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑትን አቶ ዩሱፍ ያሲንን በማነጋገር የተቀናበረው ዝግጅት ቀጥሎ ይቀርባል።

አዲሲቱ፣ ንዑሲቱ ፣ ሆኖም ፤ በቴክኖሎጂ የመጠቀችውና በዘመናዊ ጦር ኃይል የደረጀችው ሀገር እሥራኤል፤ ከተመሠረተችበት ፤ እ ጎ አ ከ 1948 ዓ ም አንስቶ፣ ከጎረቤቶቿ፣ ከዐረብ አገሮች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ከ 6 ያላነሱ ውጊያዎች ማካሄድዋ የሚታወስ ሲሆን ፤ ዋንኞቹ ጦርነቶች እ ጎ አ በ 1967 እና በ 1973 የተደረጉት ጦርነቶች ናቸው።

Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

ከ 1973 ቱ ጦርነት በኋላ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አባል ሀገራት፤ ለግብፅ ሲሉ ከእሥራኤል ጋር የነበራቸውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት አቋርጠው እንደነበረ የሚታወስ ነው። ይሁንና ግብፅ ከእሥራኤል ጋር እ ጎ አ በ 1978 የሰላም ውል ስትፈርም፣ ለብዙዎቹ የአፍሪቃ አገሮች ከእሥራኤል ጋር ግንኙነትን ለማደስ የሚያግዳቸው ሁኔታ አልነበረም። የእሥራኤልና የአፍሪቃ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ታሪክ ምን ይመስላል? የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲን--

እሥራኤል ከአፍሪቃ ጋር የነበራት ግንኙነት በሁሉም ረገድ ያማረ-የሠመረ አልነበረም። የሚያጠያይቁ፤ የሚያከራክሩ አያሌ ጉዳዮች ነበሩና--- ከብዙው በጥቂቱ --

5 የአፍሪቃን አገሮች የሚጎበኙት የአሥራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አገራቸው በአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የታዛቢነት ወንበር እንደነበራት ሆኖም በቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙኧመር ጋዳፊ ተጽእኖ ችግር ያጋጥማት እንደነበረ ከመግለጻቸውም፤ እ ጎ አ በ 2002 የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ፣የአፍሪቃ ሕብረት ከተሰኘ ወዲህ ያላገኘችውን የታዛቢነት ቦታዋን አሁን እንዲሰጣት ለማድረግ እንደሚጥሩ ነው ያስረዱት። የታዛቢነቱ ወንበር ምን ይሆን የሚያስገኘው ጥቅም?---

በግብርናም ሆነ በአጠቃላይ በሥነ ቴክኒክ ዝውውር አፍሪቃውያን ከእሥራኤል ያገኙት ጥቅም ጎልቶ የሚታይበት ሁኔታ እስከምን ድረስ ነው? ቻይና ባፍሪቃ በተንሠራፋችበት ፣ በአሁኑ ዓለም አቀፍ የንግድና የኤኮኖሚ ውድድር ዘመን አፍሪቃውያን ከሚፎካከሩ መንግሥታት የሚበጃቸውን ጥቅም ለማግኘት አያያዙን አውቀውበት ይሆን?!

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ