1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስልምና ሀይማኖት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 2 2003

«ክርስትና ያለ ጥርጥር የጀርመን ነው ። የይሁዳ ዕምነትም ያለ ጥርጥር የጀርመን ነው ። ይህ የይሁዳና የክርስትና ታሪካችን ነው ። ሆኖም አሁን እስልምናም በጀርመን ቦታ አለው ። »

https://p.dw.com/p/PcnU
ፕሬዝዳንት ቩልፍምስል picture alliance/dpa

ከአንድ ሳምንት በፊት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍ በጀርመን ውህደት በዓል ላይ የእስልምና ሀይማኖት በጀርመን ውስጥ ቦታ አለው ሲሉ ያሰሙት ይህ ንግግር ከሳምንት በላይ ጀርመናውያን ፖለቲከኞችንና ህብረተሰቡን ሲያነጋግር ከርሟል ። እንደተመረጡ በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ይበልጥ እንዲዋሀዱ ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ቩልፍ ከሶስት ወራት የስልጣን ዘመናቸው በኃላ ያስተላለፉት ይህ መልዕክት ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞችንና ለሙስሊሞች ትኩረት መሰጠቱን የሚደግፉትን ሲያስደስት ከፓርቲያቸው አንዳንድ አባላት በኩል ደግሞ ተቃውሞ አስከትሏል ።

ሂሩት መለሠ

ሸዋዬ ለገሠ