1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስረኞች ለበዓል እንደሚፈቱ በቤተሰቦች ተጠብቆ ነበር

እሑድ፣ ታኅሣሥ 29 2010

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በሰጡት መግለጫ በእስር ላይ የሚገኙ የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ግለሰቦች እንደሚፈቱ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ያልተጠበቀ ውሳኔ የተከታተሉ የእስረኞች ቤተሰቦች በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስረኞቹ ይፈታሉ ብለው ጠብቀው ነበር፡፡

https://p.dw.com/p/2qT1i
Venezuela Symbolbild Gefängnis
ምስል Getty Images/AFP/J. Barreto

እስረኞች ለበዓል እንደሚፈቱ በቤተሰቦች ተጠብቆ ነበር

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ከገዢው ግንባር አባል ፓርቲዎች ሊቀመናብርት ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ በእስር ላይ የሚገኙ የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ግለሰቦች እንደሚፈቱ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ያልተጠበቀ ውሳኔ የተከታተሉ የእስረኞች ቤተሰቦች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ እስረኞቹ ይፈታሉ ብለው ጠብቀው ነበር፡፡ አስራ አራት ዓመት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ባለቤት ያነገጋረው ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር የእስረኞች ቤተሰቦች በተስፋ እና ስጋት ቀናቶችን እየቆጠሩ ይገኛሉ ይላል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር

ተስፋለም ወልደየስ