1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራት ብይን በቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት እና ሌሎች ላይ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 2008

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ተግባር በተከሰሱ ሰባት ተከሳሾች ላይ ዛሬ ከሰባት እስከ ዘጠኝ ዓመት ፅኑ የእስራት ቅጣት በየነ። በብይኑ መሰረት፣ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ

https://p.dw.com/p/1IdRa
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

እና አቶ ዴቪድ ኦጁሉ በዘጠኝ ዓመት፣ ሌሎቹ አምስት ተከሳሾች ደግሞ በሰባት ዓመት እስራት እንዲቀጡ ታዞዋል። ብይኑ የተላለፈው የፀረ ሽብሩን ሕግ መሰረት አድርጎ ሳይሆን በመደበኛው የወንጀል መቅጫ ሕግ ነው፣ በዚህም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ላይ ቀርቦ የነበረውን የሽብር ክስ ውድቅ አድርጓል። የተከሳሾች ጠበቃ አቶ አምሀ መኮንን በብይኑ አንፃር ይግባኝ እንደሚሉ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ