1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤሉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በአዉሮጳ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2001

ፅንፈኛዉ ፖለቲከኛ የበርሊን ቆይታና ዉይይታቸዉ ከመገናኛ ዘዴዎችና ከፎቶግራፍ-አንሺዎች የተደበቀ ነበር

https://p.dw.com/p/HmKl
አቪግዶር ሊበርማንምስል picture-alliance/ dpa

አራት የአዉሮጳ ሐገራትን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት አዲሱ የእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን ትናንት በርሊን ዉስጥ ከጀርመን ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግረዋል።ሊበርማን ከበርሊን በፊት ሮምና ፓሪስን ጎብኝተዉ ነበር።ዛሬ ደግሞ ፕራግን ይጎበኛሉ ተብሏል።በየደረሱበት ሕዝባዊ የተቃዉሞ ሠልፍ፥ ዉግዘትና ትችት የገጠማቸዉ ቀኝ ፅንፈኛዉ ፖለቲከኛ የበርሊን ቆይታና ዉይይታቸዉ ከመገናኛ ዘዴዎችና ከፎቶግራፍ-አንሺዎች የተደበቀ ነበር።የሊበርማንን ጉብኝትና የተደበቀበትን ምክንያት ይልማ ሐይለሚካኤል ከዚያዉ ከበርሊን ተከታትሎታል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ