1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤልና የፍልስጤም ድርድር

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2005

የፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስ ፅሕፈት ቤት «ለድርድሩ ትልቅ እንቅፋት» ባለዉ የሠፈራ መንደር ግንባታ ላይ ሁለቱን ወገኖች የምታደራድረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ግልፅ እንድታሳዉቅ ጠይቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ የመንግሥታቸዉን ግልፅ አቋም ግልፅ ማድረጋቸዉ አልቀረም።

https://p.dw.com/p/19PvQ
ARCHIV - Palästinensische Angehörige fordern am 17.04.2007 in Ramallah, Palästina, die Freilassung ihrer Verwandten, die in israelischen Gefängnissen festgehalten werden. Am 13.08.2013 sollen palästinensische Langzeithäftlinge in Israel freigelassen werden. Foto: EPA/ALAA BADARNEH (zu dpa «Thema Freilassung palästinensischer Langzeithäftlinge» vom 12.08.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++ pixel
ፍልስጤማዉያን፤ እስረኞች እንዲፈቱ ሲጠይቁምስል picture-alliance/dpa

የእስራኤልና የፍልስጤም ባለሥልጣናት በቅርቡ እንዳዲስ የጀመሩትን የሠላም ድርድር ዛሬ ይቀጥላሉ።እስራኤል ትናንት ባንድ በኩል «ለድድሩ መቃናት» በሚል የፍልስጤም እስረኞችን ስትፈታ በሌላ በኩል በሐይል በያዘችዉ ግዛት ተጨማሪ የአይሁድ ሠፈራ መንደሮች ለመገንባት ወስናለች።ፍልስጤሞች የእስረኞቹን መፈታት በደስታ ሲቀበሉት፥ አንዳድ እስራኤላዉያን ተቃዉመዉታል።እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የፍልስጤም ግዛት አዲዳሲስ የአይሁድ ሠፈራ መንደሮች ለማስገንባት መወሰንዋን ደግሞ ፍልስጤሞች አዉግዘዉታል።በእስራኤል ተቃራኒ እርምጃዎች የታጀበዉ ድርድር ከአግባቢ ዉጤት መድረሱ ብዙዎችን አጠራጥሯል።

የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መንግሥት ለድርድሩ መሳካት «ቀና ምልክት» ባለዉ እርምጃዉ ሊፈታቸዉ ካቀደዉ አንድ መቶ አራት ፍልስጤማዉያን እስረኞች የመጀመሪያዎቹ ትናንት ተለቀዋል።ሃያ-ስድስት ናቸዉ።ለእስራኤል መንግሥት የ«ቀና ምልክት» ተምሳሌት የሆኑት እስረኞች ለእስራኤሎች ቢያንስ እስከ ትናንት አሸባሪ ወይም ነብሰ ገዳይ ነበሩ።

የእስረኞቹን መፈታት በመቃወም ትናንት ቴል አቪቭ አደባባይ ተሰልፈዉ ለነበሩት እስራኤላዉያን ደግሞ እስረኞቹ አሁንም ነብሰ ገዳይ ናቸዉ።

የእስራኤል መንግሥት እነሱን መልቀቁ የዛሬ-ሠላሳ ዓመት አማቻቸዉ በፍልስጤሞች የተገደለባቸዉ አየለት ተማም እንደሚሉት-ትልቅ ጥፋት ነዉ።

«የመንግሥታችንን ዉሳኔ ለመቀበል አልተዘጋጀሁም።ለምድን ነዉ እነዚሕን እጃቸዉ ደም ያለባቸዉን ገዳዮች የምንለቀዉ።ከማሕሙድ አባስ ጋር በጤረጳዛ ዙሪያ ተቀምጠን ሥለ ሠላም ለመነጋገር ነዉ? እነዚሕ ሰዎች በሙሉ እጃቸዉ በደም ተነክሯል።»

ለፍልስጤሞች ባንፃሩ ጀግኖች ናቸዉ።ትናንት ከተለቀቁት ሃያ-ስድስት እስረኞች አስራ-አንዱ ከፍልስጤሙ ራስ-ገዝ መስተዳድር ሙቃታዓ ቤተ-መንግሥት ድረስ ተጋብዘዉ የጀግና አቀባበል ተደረጎላቸዋል።«ይሕ የመጀመሪያዉ ቡድን ነዉ።» አሉ የራስ ገዙ መስተዳድር ፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስ ለአቀባበሉ ፌስታ ለታደመዉ ሕዝብ «ፍልስጤማዉያን በሙሉ ከእስራኤል እስር ቤት እስኪለቀቁ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።»

ብዙ ጊዜ ከሐዘን፥ ወይታ ለቅሶ፥ ፉከራ-ዛቻ በስተቀር ደስታ ፌስታ የማታዉቀዉ ረመለሕ ትናንት ዕኩሌት በርግጥ ፈነደቀች።ለሃያ-ስምንት ዓመቱ ወጣት ለአላዓ ሻዓት ደስታዉ ልዩ ነዉ።አባቱን ዳግም አየ።

«ይሕን አጋጣሚ ድፍን ሃያ-አንድ ዓመት ጠብቄያለሁ።አንድ ሚሊዮን ዓመት የሆነዉ ነዉ-የመሰለኝ።ልጅ ሆኜ አባቴ ተለየኝ።አሁን ዳግም አገኘሁት።ሃያ-ስምንት አመቴ ነዉ።ግን የሰባት ዓመት ልጅ የሆንኩ ያሕል ነዉ-የሚሰማኝ።»

የእስራኤል መንግሥት የፍልስጤሞች ደስታ-በሐዘን፥ የእስራኤልን «ቀና ርምጃ»-በአወዛጋቢ ዉሳኔ፥ የድርድሩ የሩቅ ተስፋ-በቀቢፀ ተስፋ ለመጣፋት አፍታ አልፈጀበትም።የቤቶች ሚንስትር ኡሪ አርየል መንግሥታቸዉ በሐይል በያዘዉ የፍልስጤሞቹ ግዛት ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዘጠኝ መቶ አርባ-ሁለት አዳዲስ የአይሁድ መኖሪያ ቤቶች ለማስገንባት መወሰኑን አስታወቁ።

የእስራኤል ፍስልጤሞች ድርድር ላለፉት ሃያ-ዓመታት እየተጀመረ ለመቋረጡ፥ እየታቀደ ለመሰረዙ፥ እየታሰበ ለመምከኑ-እንደ ዋና ምክንያት ከሚጠቀሱት አንዱ እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የፍልስጤሞች ግዛት የአሁድ ሠፈራ መንደር መገንባቷን አለማቆምዋ ነዉ።የፍልስጤም ነፃ አዉጪ ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣን ያሲር አብድ ረቦ እንዳሉት አዲሱ የእስራኤል ዉሳኔም ገና በቅጡ ያልተጀመረዉን የሠላም ድርድር ሊያደናቅፈዉ ይችላል።

የፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስ ፅሕፈት ቤት «ለድርድሩ ትልቅ እንቅፋት» ባለዉ የሠፈራ መንደር ግንባታ ላይ ሁለቱን ወገኖች የምታደራድረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ግልፅ እንድታሳዉቅ ጠይቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ የመንግሥታቸዉን ግልፅ አቋም ግልፅ ማድረጋቸዉ አልቀረም።

«ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉንም ሠፈራ መንደሮች በሕገ-ወጥነት ነዉ-የምታየዉ።ይሕ የዩናይትድ ስቴትስ መርሕ ነዉ።ይሕን መርሐችንን ለእስራኤል ወዳጆቻችን በግልፅ አሳዉቀናል።የወደፊቱ ጉዞ ምን እንደሚመስልም ሁሉም ወገን እንዲረዳዉ ለማድረግም ከፍልስጤሞች ጋር በቅርብ ጥረናል።ይሕ የሚያመለክተዉ ባስቸኳይ ወደ ጠረጤዛዉ ድርድር ባስቸኳይ መመለስ አስፈላጊ መሆኑን ነዉ።»

ኬሪ ሥለ ጉዳዩ ከማሕሙድ አባስ ጋር በስልክ መነጋገራቸዉ ተዘግቧል።የእስራኤሉ የቤቶች ሚንስትር ኡሪ አርየል መልስ ግን «የት መገንባት እንዳለብን ማንም ሊነግረን አይችልም።» የሚል ነዉ።የዛሬዉ ድርድር የሚጀመርበት ሰዓት ሲሰላ የእስራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ ዉስጥ የሮኬት ማወንጨፊያ ሥፍራዎች ያላቸዉን አካባቢዎች በጄት ደበደቧል።ጦሩ አካባቢዉን የደበደበዉ የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች የተኮሱት ሮኬት ሳድሮት በተባለ አካባቢ ማረፉ ከተነገረ በኋላ ነዉ።

A freed Palestinian prisoner celebrates upon his arrival in the West Bank city of Ramallah early August 14, 2013. Israel freed 26 Palestinian prisoners on Wednesday to keep U.S.-sponsored peacemaking on course for a second round of talks, but diplomacy remained dogged by Israeli plans for more Jewish homes on land the Palestinians claim for a future state. REUTERS/Ammar Awad (WEST BANK - Tags: POLITICS)
ፌስታ-እስረኞች ተለቀቁምስል Reuters
FILE - A general view of the construction site of a housing unit in the West Bank settlement of Al-Karmel south of Hebron, 08 July 2013. EPA/ABED AL HASHLAMOUN (zu dpa "Ärger mit Ansage: EU-Boykott von Siedlungen empört Israel" vom 16.07.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ከአይሁድ ሰፈራ መንደሮች አንዱምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ