1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ሃማስ ፍጥጫ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 10 2006

የእስራኤል ጦር ኃይል በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ የታገቱ ሶስት ወጣት እስራኤላዉያንን ለማስለቀቅ ናቡስ የተባለችዉን ከተማና አካባቢዉን ወርሮ የተጠናከረ ፍተሻ ማካሄዱን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/1CKKS
Israel Soldaten Jugendliche Hamas
ምስል Reuters

የእስራኤል መንግስት ወጣቶቹን ያገተዉ ሃማስ ነዉ ቢልም ሃማስ በበኩሉ ቀኝ አክራሪ እስራኤላዉያን ድርጊቱን በእሱ ለማሳበብና ከፋታህ ጋ ከመሠረተዉ የጥምር መንግስት ለማስወጣት አቀነባብረዉታል ሲል አጣጥሏል። የእስራኤል ወታደሮች ወደሁለት መቶ የሚገመቱ አብዛኞቹም የሃማስ አባላት የሆኑ ፍልስጤማዉያንን በዚሁ ምክንያት ማሠራቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል አመልክቷል። በፍልስጤም እስራኤል መካከል ቀጣይ የሰላም ድርድር በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት የተፈጠረዉ ይህ አጋጣሚም አካባቢዉን ለሌላ ግጭት ጦርነት ዳርዳር እያለዉ እንደሚገኝ ሃይፋ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ግርማዉ አሻግሬ ገልጾልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ግርማዉን በስልክ ስለሁኔታዉ አነጋግሬዋለሁ።

ግርማዉ አሻግሬ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ