1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ምርጫና የኔትናያሁ ድል

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2007

እስራኤል ባካሄደችዉ ብሔራዊ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ድል እንደቀናዉ ዛሬ ማለዳ ተሰምቷል። የመራጬ ድምፅ 90 በመቶ ተቆጥሮ ባለበት ሁኔታም ከወዲሁ ሊኩድ ፓርቲ የምክር ቤቱን 30 መቀመጫዎች እንደሚይዝ ተገምቷል።

https://p.dw.com/p/1Esnb
Israel Wahlen 2015 Likud Anhänger Jubel
ምስል Reuters/A. Cohen

የኔንታንያሁ ተቀናቃኝ ግራ ዘመሙ የፅዮናዉያን አቀንቃኝ አይዛክ ሄርዞግ ፓርቲ በአንፃሩ 24 መቀመጫዎችን ሊያገኝ እንደሚችል ተገልጿል። ኔትንያሁ በአንዳንዶች ቢወደዱም በተቃራኒዉ ዳግም መመረጣቸዉ ለብዙዎች አስደንጋጭ ዜና ነዉ የሆነዉ። በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ለሚካሄደዉ የሰላም ድርድር እንደእንቅፋት የሚታዩት ኔታንያሁ በዚሁ ምክንያት በተለይ በአረቡ ዓለም እጅግም ተቀባይነት እንደሌላቸዉ ነዉ የሚነገረዉ። ኢራን የእሳቸዉ መመረጥ ምንም ለዉጥ እንዳይኖር ያደርጋል ስትል፤ የፍልስጤም መሪ ማሕሙድ አባስ በበኩላቸዉ የሁለት መንግሥት ሃሳብን ከሚቀበል የእስራኤል መንግሥት ጋ አብረዉ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል። የኔታንያሁ ዳግም መመረጥ በአረቡ ዓለም የፈጠረዉ ስሜት ምን ይመስላል ለሚለዉ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ወደጄዳ ደዉዬ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን በአጭሩ አነጋግሬዋለሁ።

ነብዩ ሲራክ/ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ