1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ርምጃ እና የአፍሪቃውያን ተቃውሞ

ቅዳሜ፣ ጥር 3 2006

የእስራኤል መንግሥት አዲስ ያወጣውን የስደተኞች ሕግ እና በስደተኞች ላይ የሚያደርሰዉን በደል በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ሰሞኑን በተከታታይ የአደባባይ ሠልፍ ሲያካሂዱ ሰነበቱ።

https://p.dw.com/p/1ApA9
Afrikanische Flüchtlinge demonstrieren in Israel
ምስል Reuters

የእስራኤል ምክር ቤት ክኔሰት አዲስ አሻሽሎ ባፀደቀው ሕግ መሠረትበሕገ ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል የገቡ አፍሪቃዉያን ስደተኞች በማከማቻ ጣቢያ መስፈር እና ጣቢያዉ ዉስጥ መኖራቸዉን በቀን ሦስት ጊዜ እየፈረሙ ማረጋገጥ ይገባቸዋል። ይህን ካላደረጉ ያለ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ለአንድ ዓመት ያህል ይታሰራሉ።

ስደተኞቹ እና የመብት ተሟጋቾ ካለፈዉ ሁድ ወዲህ በቴል አቪቭ በሚገኙ የዉጪ ኤምባሲያዎች፥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት በኢየሩሳሌም በሚገኘው የሀገሪቱ ምክር ቤት፣ ክኔሰት እና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ፊት ለፊት ተገኝተዉ ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል።

Afrikanische Flüchtlinge demonstrieren in Israel
ምስል Reuters

እስራኤል ውስጥ በወቅቱ ወደ 60,000 የሚጠጉ፣ በብዛት ከኤርትራ እና ከደቡብ ሱዳን የሄዱ ስደተኞችን የሚኖሩ ሲሆን፣ የእስራኤል መንግሥት ስደተኞቹን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለአንድ ዓመት ለማያቀደበትን እና ማይመቹ ማቆያ ጣቢያዎች በግዴታ ስፈሩን ደተኞቹ እና የመብት ተሟጋቾችን አብዝቶ አስቆጥቶዋል። ስደተኞቹ የመስራት ፈቃድ እንዲሰጣቸው እና የተገን መጠየቂያ ማመልከቻቸውን እንዲታይላቸው ነው እየጠየቁ ያሉት። ይሁንና፣ እስራኤል ስደተኞቹን እንደ ተገን ጠያቂዎች ሳይሆን ለሀገሯ ፀጥታ ስጋት የሚደቅኑ አድርጋ የምትመለከታቸው። የገዢው የሊኩድ ፓርቲ አባል እና በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ኤማኑዌል ዳፎን ይህን የእስራኤል አቋም ትክክለኛ ነው ይላሉ።

« ተገን ጠያቂ ስደተኞች አይደሉም፣ በሕገ ወጥ መንገድ እና በ ድብቅ የእስራኤል ድንበር ጥሰው የገቡ እና ተገን እንዲሰጣቸው የጠየቁ ናቸው። »

Afrikanische Flüchtlinge demonstrieren in Israel
ምስል Reuters

ሕገ ወጥ ያላቸውን ስደተኞች ከሀገሩ ለማስወጣት የጀመረውን ርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ያስታወቀው የእስራኤል መንግሥት ለስደተኞቹ 3,500 ዶላር እየሰጠች ወደ ሀገራቸው በፈቃዳቸው እንዲመለሱ ለማበረታታት ባነቃቃችው ርምጃ መሠረት፣ 2,600 የሚሆኑ ስደተኞች ባለፈው አውሮጳውያኑ 2013 ዓም ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ገልጾዋል።

ስደተኞቹ፣ አንዳንዶቹም እስራኤል ውስጥ አምስት ዓመት የኖሩትና በድብቅ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈለው ስራ ላይ የሚገኙት ኤርትራውያኑ እና ደቡብ ሱዳናውያኑ ክትትል ሸሽተው የተሰደዱ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ይህንን የእስራኤል ሀሳብ እንደማይቀበሉት እና ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

« ለምን ወደ እስራኤል መጣሁ እያልኩ ነው ራሴን የጠየቅሁት። እስራኤል እንዲህ ታደርገኛለች ብዬ ባስብ ኖሮ አልመጣም ነበር፣ እስራኤል እኛን ለሀገሯ ፀጥታ ስጋት የሚደቅንንን ሰርጎ ገቦች ብላ ነው የምትጠራን፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ እኛ ሰርጎገቦች አይደለንም፣ ስደተኞች ነን። »

አንዱ ኤርትራዊ ስደተኛ እንዳለው፣ ጥያቄአቸው ሰሚ እስኪያገኝላቸው ድረስ የአደባባይ ተቃውሞአቸውን ይቀጥላሉ።

የእስራኤል መንግሥትን ርምጃ የመብት ተሟጋቾች፣ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት፣ በምሕፃሩ «ዩኤንኤችሲአር» በጥብቅ ተቃውመውታል። እአአ በ1948 ዓም ከተመሠረተችበት አንስቶ እስከዛሬ ድረስ 200 ስደተኞችን ብቻ እንደ ተገን ጠያቂዎች የተቀበለችው እስራኤል የተመድ የስደተኞችን ተገን አሰጣጥ ፖሊሲን እንደጣሰች እና ዘረኝነትን የሚያንፀባርቅ መከራከሪያ ሀሳብ እንደምታቀርብ የመብት ተሟጋቹ ሚሼል ቫርሻቭስኪ አስታውቋል።

« እስራኤል ስደተኞች የተገን ማመልከቻቸው መልስ እስኪያገኝ ድረስ በሀገሯ መቆየት የሚችሉበትን መብት ጥሳለች። ባንዳንድ የእስራኤል ትላልቅ ከተሞች ሰፈሮች ውስጥ እስራኤል ሕገ ወጥ የምትላቸው ስራ ብለው የፈለሱት ብቻ ሳይሆኑ ጥቁሮች ሁሉ ለሀገሪቱ የፀጥታ አደጋ እንደደቀኑ ነው የሚቆጠሩት። »

ቤንጃሚን ኔታንያሁ የሚመሩት መንግሥት ግን እስካሁን በአፍሪቃውያኑ ስደተኞች አኳያ የያዘውን አቋም ለመቀየር ዕቅድ እንደሌለው ነው ያመለከተው።

አርያምተክሌ

ማንተጋፍቶትስለሺ