1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል የአየር ጥቃት ቁጣ አስነሳ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2001

የእስራኤል ታንኮች፣ ወታደራዊ ከባድ ተሽከርካሪዎችና የጦር ሠራዊቱ ወደ ጋዛ ተጠግተው ለጊዜው በአየርና በባሕር የሚደረገውን ጥቃት ወደ ሙሉ ጦርነት ሲያሻግረው ሊቀላቀሉ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነውም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/GPMI
ጋዛ ስትነድ
ጋዛ ስትነድምስል AP
እስራኤል ከጦር እውሮፕላኖቿ በምታዘንበው የቦንብ ጥቃት የፍልስጥኤሟ ጋዛን ስትደበድብ አራተኛ ቀኗ መዳረሱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። የሟቾቹ ቁጥር በትንሹ ሶስት መቶ ስልሳ ደርሷል። ጥቃቱ በበርካታ የአረብ አገራት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል። እስራኤል ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሶ የሮኬት ጥቃቶችን በማድረስ ስለተዳፈረኝ ለሳምንታት የሚዘልቀው የአየር ጥቃት ገና በምድርም ይቀጥላል ስትል ገልፃለች።