1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሎፍ ፓልመ ሽልማት ለኮንጎ ዶክተር

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2001

በዴምክራቲክ ኮንጎ ተገደዉ የሚደፈሩ ሴቶች በስለት ወይ በጥይት ተጨማሪ ጉዳት በሆዳቸዉ የታችኛዉ ክፍል ላይ ይፈፀምባቸዋል።

https://p.dw.com/p/GmcV
...ሕፃኗ ሕፃን አዝላ...
...ሕፃኗ ሕፃን አዝላ...ምስል AP

የጥቃቱ ዓይነት እንደ አማፅያኑ ስልት ይለያያል። የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች የህክም እርዳታ የሚያደርገዉ ሃኪም ቤት ከአስር ሺ በላይ ለሆኑት ህክምና አድርጓል። ሃኪም ቤቱን በማቋቋም ይህክምና ርዳታዉን እየሰጡ የሚገኙት ኮንጓዊዉ ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጌ የጎርጎሮሳዊዉን 2008ዓ,ም የክብር ሽልማት ስዊድን ላይ ተቀብለዋል።