1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሕዴድ ሹም ሽር

ረቡዕ፣ መስከረም 11 2009

የፖለቲካ ተንታኝና የተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣን ግን ሹም ሽሩ የሕዝቡን ቅሬታና ተቃዉሞ ለመመለስ መፍትሔ አይሆንም ባይ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1K644

[No title]

ካለፈዉ ሕዳር ጀምሮ ተቃዉሞ፤ግጭትና ግድያ የተጠናከረበትን የኦሮሚያ ክልልን የሚያስተዳድረዉ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ የእስካሁን ሊቀመንበሩንና ምክትል ሊቀመንበሩን ሽሮ ሌሎች ሾሟል።ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ የፓርቲዉ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ መስተዳድር ፕሬዝደንት የነበሩት አቶ ሙክታር ከድርና የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበርና የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ወይዘሮ አስቴር ማሞ በሌሎች የተተኩት ሥልጣናቸዉን በፈቃዳቸዉ በመልቀቃቸዉ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ያነጋገራቸዉ የፖለቲካ ተንታኝና የተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣን ግን ሹም ሽሩ የሕዝቡን ቅሬታና ተቃዉሞ ለመመለስ መፍትሔ አይሆንም ባይ ናቸዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ