1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ተቃዉሞና የሰብዓዊ መብት ድርጅት ጥሪ

ሰኞ፣ ጥር 2 2008

ባለፉት ሁለት ወራት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች በተፈጠረው የተማሪዎች ተቃውሞ 140 ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ መቀመጫውን በኒውዮርክ ከተማ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት Human Rights Watch ገልጿል።

https://p.dw.com/p/1HbZn
Human Rights Watch Logo

[No title]

ድርጅቱ ከወር በፊት ይፋ አድርጎት የነበረው የሟቾች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩንም አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ ወደ አጎርባች የኦሮሚያ ከተሞች እንዲስፋፋ ያደርግሆናል በሚል የተቀጣጠለው የማስተር ፕላን ተቃውሞ ከምርጫ 97 ወዲህ በሀገሪቱ የተከሰተ ከፍተኛ ቀውስ መሆኑንም Human Rights Watch በመግለጫው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ መንግስት ለተማሪዎቹ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ እና በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ድርጅቱ ጥሪ አቅርቧል።

ናትናኤል ወልዴ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ