1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ አመታዊ የመርህ ንግግር

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2005

የአሜሪካንን ምጣኔ ሃብት ለማሳደግ ሃገሪቱ ከፍተኛ የቴክኒክ ሙያ እውቀት ያላቸውን የውጭ ዜጎች መሳብ መቻል እንዳለባትም አሳስበዋል ። ሃገሪቱ ተስጥኦና ብሩህ ተስፋ ያላቸውን ስደተኞች በመቀበል ምጣኔ ሃብትዋን ማጠናከር እንደሚገባትም ጠቁመዋል ።

https://p.dw.com/p/17dhU
GettyImages 161606978 President Barack Obama, flanked by Vice President Joe Biden and House Speaker John Boehner of Ohio, gestures during the State of the Union address before a joint session of Congress on Capitol Hill in Washington, Tuesday Feb. 12, 2013. AFP PHOTO / Pool / Charles Dharapak (Photo credit should read CHARLES DHARAPAK/AFP/Getty Images)
ምስል AFP/Getty Images

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ለመፈፀም ያቀዷቸውን ተግባራት ከግብ ለማድረስ የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጭ ና ህግ አስፈፃሚ ምክር ቤት አባላት ድጋፍ እንዲሰጧቸው ጠየቁ ። ኦባማ ትናንት ለ 2ቱ ምክርቤቶች ተጣማሪ ጉባኤ ባሰሙት አመታዊ የመርህ ንግግራቸው የግብር ማሻሻያ ህግ እንዲወጣ ፣ የግለሰቦች የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ና የፍልሰት ጉዳዮች ህጎች እንዲሻሻሉ እንዲሁም ዝቅተኛው ክፍያ እንዲጨምር ጠይቀዋል ። አፍጋኒስታን ከሚገኘው የአሜሪካ ጦር ግማሹ በጎርጎሮሳውያኑ 2014 አም መጀመረያ ላይ ወደ ሃገሩ እንደሚመለስም አስታውቀዋል ። ሂሩት መለሰ ዝርዝር ዘገባ አላት ።

U.S. President Barack Obama (C), flanked by Vice President Joe Biden (L) and House Speaker John Boehner (D-OH), delivers his State of the Union speech on Capitol Hill in Washington, February 12, 2013. REUTERS/Charles Dharapak/Pool / Eingestellt von wa
ምስል Reuters

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ አመታዊው የመርህ ንግግር ይበልጡን ያተኮረው በሥራ ፈጠራ ፣ የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዲጠናከር በተከናወኑት ተግባራትና መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ነበር ። ኦባማ የአሜሪካን ምጣኔ ሃብት እንዲያንሰራራ በተወሰዱት እርምጃዎች ተጨማሪ የሥራ እድሎች እንደተፈጠሩ ጠቅሰው አሁንም ቢሆን ግን በርካታ አሜሪካውያን አስተማማኝ ሥራ ማግኘት አለመቻላቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም ።

« ለጠንካራ ሥራቸው ና ለቁርጠኝነታቸው ዋጋ ያልተከፋላቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን እንዳሉ እዚህ የተሰበሰብነው እናውቃለን ። ኤኮኖሚያችን የሥራ እድል እንዲጨምር አድርጓል ሆኖም በርካታ ሰዎች ቋሚ ሥራ ማግኘት አልቻሉም ። የትላልቅ ኩባንያዎች ትርፍ ወደ ላይ ቢተኮስም ላለፉት አሥርታት ደሞዝና ገቢ ብዙ አላደገም ። እውነተኛውን የአሜሪካን የምጣኔ ሃብት እድገት ማንቀሳቀስ የኛ ትውልድ ሃላፊነት ነው ። ያም ማለት የሚያድግና የሚንሰራፋውን መካከለኛውን መደብ ማውጣት ነው ።»

Overall view as U.S. President Barack Obama (R) delivers his State of the Union speech on Capitol Hill in Washington, February 12, 2013. REUTERS/Jason Reed / Eingestellt von wa
ምስል Reuters

ኦባማ በአሜሪካን በሰዓት የሚተመነው ዝቅተኛ ክፍያ ከ 7 ዶላር ከ 25 ሳንቲም ወደ 9 ዶላር ከፍ እንዲል በትናንቱ የመርህ ንግግራቸው ጠይቀዋል ። ሃገሪቱን ለምጣኔ ሃብት ችግር የዳረገውን ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ለማስተካከል የሚወሰዱትን የበጀት ቅነሳ እርምጃዎች መጥፎ ሃሳብ ሲሉ ያጣጣሉት ኦባማ የተመጣጠነ የበጀት ቅነሳን በአማራጭ መፍትሄነት ጠቁመዋል ። ኦባማ እንዳሉት በ 10 አመታት ውስጥ የሃገር ውስጥ ገቢ በ 600 ቢሊዮን ዶላር እንዲጨመር በማድረግ የተለጠጠውን የአሜሪካንን የበጀት ጉድለት መቆጣጠር ይቻላል ። የአሜሪካንን ምጣኔ ሃብት ለማሳደግ ሃገሪቱ ከፍተኛ የቴክኒክ ሙያ እውቀት ያላቸውን የውጭ ዜጎች መሳብ መቻል እንዳለባትም አሳስበዋል ። ሃገሪቱ ተስጥኦና ብሩህ ተስፋ ያላቸውን ስደተኞች በመቀበል ምጣኔ ሃብትዋን ማጠናከር እንደሚገባትም ጠቁመዋል።

«መካከለኛውን መደብ እንዲያድግ ዜጎቻችን የዛሬዎቹ ሥራዎች የሚጠይቁትን ትምሕርት እና ሥልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል ። ሆኖም አሜሪካ ጠንክሮ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ የማደግ እድል የሚያገኝባት ስፍራ መሆንዋን ማረጋገጥ መቻል አለብን ። የአስተዋይ ታታሪና ባለብሩህ ተስፋ ስደተኞችን ተሰጥዖ ከተጠቀምንበት ምጣኔ ሃብታችን ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል ። በአሁኑ ቅፅበት የንግድ የሥራ የህግ አስከባሪ ክፍሎች እንዲሁም የልዩ ልዩ እምነት ተከታይ ማህብረሰቡ ክፍሎች ሁሉም የሚስማሙት አጠቃላይ የስደተኞች አያያዝ ህግ ማሻሻያው ጌዜው አሁን መሆኑን ነው። »

U.S. President Barack Obama (C) starts to deliver his State of the Union Speech as Vice President Joe Biden (rear, L) and House Speaker John Boehner (R-OH) (rear, R) listen on Capitol Hill in Washington, February 12, 2013. REUTERS/Kevin Lamarque / Eingestellt von wa
ምስል Reuters

የስደተኞችን አያያዝ የሚመለከት ረቂቅ ህግ በመቀረፅ ላይ መሆኑን ያወደሱት ኦባማ ህጉ እንደደረሳቸው ወዲያውኑ በፊርማቸው ለማፅደቅም ቃል ገብተዋል ። ከአሜሪካን ምጣኔ ሃብትና ከስደተኞች ጉዳይ በተጨማሪ ኦባማ አፍጋኒስታን ከዘመተው የአሜሪካን ጦር ገሚሱ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ሃገሩ ይመለሳል ብለዋል።

«33 ሺህ ጀግኖች ወንዶችና ሴቶች ወታደሮቻችንን ወደ ሃገራቸው መልሰናል በዚህ ፀደይ የአፍጋኒስታን ወታደሮች የመሪነቱን ቦታ ሲይዙ የኛ ኃይሎች ደግሞ ወደ ድጋፍ መስጠቱ ትልዕኮ ይዞራሉ። በሚቀጥለው አመት ሌሎች 34 ሺህ የአሜሪካን ወታደሮችን ከአፍጋኒስታን ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ። ይህ ቅነሳም ይቀጥላል ። በመጪው አመት መጨረሻም በአፍጋኒስታን የምናካሂደው ጦርነት ያበቃል»

ኦባማ በአመታዊ የመርህ ንግግራቸው ለአካባቢ ጥበቃ እገዛ የሚያደርጉ እርምጃዎችን እንደሚወስዱም አስታውቀዋል።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ