1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ እና የነታንያሁ ውይይት

ረቡዕ፣ ሰኔ 30 2002

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ የመከከለኛውን ምስራቅ የሰላም ድርድር በአዲስ መንገድ እንዲጀመር መስማማታቸውን አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/OD9a
ኦባማ እና ነታንያሁምስል AP

ትናንት ዋይት ሀውስ ውስጥ የመከሩት ሁለቱ መሪዎች በእስራኤልና በፍልስጤም መሪዎች መካከል ተከታታይና ቀጥተኛ የሰላም ድርድር እንደሚጀመርም ጠቁመዋል ። ነታንያሁና ኦባማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዚህ ቀደም ቀዝቅዟል የተባለው የእስራኤልና የአሜሪካን ግንኙነት እጅግ ጠንካራ እንደሆነ አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ