1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ ዳግም መመረጥ እና የአፍሪቃ ተስፋ

ዓርብ፣ ጥቅምት 30 2005

ኦባማ ባለፉት አራት አመታት አፍሪቃውያን ተስፋ የጣሉባቸውን ያህል አፍሪቃን ሲረዱ አልታዩም። ኦባማ በመጪው አራት አመታት ለአፍሪቃ የሚኖራቸው ተስፋ ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/16f9I
US President Barack Obama (R) smiles as he walks with First Lady Michelle Obama (2nd L) through a line of dancers during a departure ceremony in Accra, Ghana, July 11, 2009. AFP PHOTO/Jim WATSON (Photo credit should read JIM WATSON/AFP/Getty Images)
ምስል AFP/Getty Images

የዮናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዳግም በፕሬዚዳንትነት ተመርጠዋል። የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ዘመቻውን እና የምርጫውን ውጤት በሀገራቸው ምርጫ እንደተካሄደ ማለት ይቻላል በቀጥታ ሲያሰራጩ ተስተውሏል። ኦባማ ከአራት አመት በፊት ሲመረጡ በተለይ ለአፍሪቃውያን ትልቅ ተስፋ ጥለውባቸው ነበር። በአሁንስ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች  ያደረባቸው ስሜት ምን ይመስላል? ሶስት ወጣቶችን አነጋግረናል።

ሌሎች ወጣቶችም በኦባማ ዳግም መመረጥ ያላቸው አስተያየት በፊስ ቡክ አካፍለውናል። ደስ አለኝ የተባለ አንናቢያችን፤ «ኦባማ የ300 ሚሊዮን ተስፈኞች እንጂ የአፍሪቃ አይደሉም» ይላል። ሰለሞን ተክሌ ደግሞ የኦባማ ዳግም መመረጥ ለUSA ህዝብ ጥሩ ጊዜ እና አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያለው። ይሄውም ጀምረውት ለነበረው ውጥን ስራ ብሩህ ወቅት ነው፤ አፍሪቃም የሆነ ቁምነገር ከሳቸው ትጠብቃለች ሲል አስተያየቱን ገልጿል። ደመቀ ፍሰሀ ደግሞ «ኦባማ ለአፍሪቃ ጥሩ ነገር ያደርጋሉ ብሎ ማሰብ ከንቱ ተስፋ ስለሆነ ባንለፋ ጥሩ ነው። የአፍሪቃ ችግር የሚፈታው በልጆቿ ብቻ ነው» ብሏል።አዳነ ሳሙኤል ፤«የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ማንም ይሁን ማን ለአፍሪቃ የተለየ ነገር አይፈጥሩም። ለዕርዳታ ከሆነ ከአፍሪቃ የሚጠበቀው ፀባይ ማሳመር ብቻ ነው፤ ነው ያለው። በርካታ አስተያየት የሰጡን የኦባማ መመረጥ ለአፍሪቃ ምንም አይነት ለውጥ አያመጣም ነው ያሉት። ሁሉንም አስተያየቶች ከፌስ ቡክ ገፃችን dw amharic  ላይ ማንበብ ይቻላል። የድምፁን ዘገባ ወደታች ሲመለከቱ ያገኙታል።

Villagers ride motorcycles and wave branches to celebrate Obama's re-election, in the village of Kogelo, home to Sarah Obama the step-grandmother of President Barack Obama, in western Kenya Wednesday, Nov. 7, 2012. (Foto:Ben Curtis/AP/dapd)
ኬንያውያን በኦማባ ዳግም መመረጥ ሲደሰቱምስል dapd

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ