1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦብነግ ማስተባበያ

ሰኞ፣ ግንቦት 2 2002

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባለፈዉ ሳምንት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጭ ግንባር ሁለት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ከፍተኛ ኃላፊዎችን እንደገለደለ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/NKTc
ምስል picture alliance/dpa

ሌሎች በርካታ የግንባሩን ተዋጊዎች በቁጥጥር ስር እንዳዋለም። አስታዉቋል። ኦብነግም በመጪዉ የግንቦቱ ምርጫ እንደሚሳተፍ፤ ከመንግስትም ጋር እየተደራደረ ነዉ የሚሉ ዘገባዎች ተሰምተዋል። እነዚህን ጉዳዮች በማንሳት ጥያቄ የቀረበለት ኦብነግ ዘገባዎቹን አስተባብሏል። ወደሎንዶን በመደወል የግንባሩን የዉጭ ግንኙነት ያነጋገረዉ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

መሳይ መኮንን ፣ ሸዋዬ ለገሰ

ሂሩት መለሰ