1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦብነግ ባለሥልጣናት በኬንያ ታፈኑ መባሉ

ማክሰኞ፣ ጥር 27 2006

ሁለት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ የ«ኦብነግ» ባለሥልጣናትን አግተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት የኬንያ ፖሊሶች በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሠረተባቸዉ የመዲናይቱን ናይሮቢ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ክፍልን ጠቅሶ አዣንስ ፍራን ፕሪስ ዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/1B2fC
Nairobi Skyline Kenia Stadtansicht
ምስል Fotolia/Natalia Pushchina

ታፍነዉ ተስደዋል የተባሉት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ «ኦብነግ» ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ኬንያ ያቀኑት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለሰላም ድርድር ላይ ለመካፈል እንደነበር ተጠቅሶአል። ።

Nomadin hütet Ziegen in Äthiopiens Krisenregion Ogaden
ምስል picture alliance/dpa

በፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ መሰረት፤ ሁለቱ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፤ ኦብነግ መልክተኞች ሱሉብ አብዲ አህመድ እና አሊ መሃመድ ሁሴይን እሁድ ጥር 18 በናይሮቢ ከተማ በሚገኝ ከአንድ ምግብ ቤት አጠገብ በሁለት ኬንያዉያን ወታደሮች፤ ታፍነዉ ተወስደዋል። አፈናዉን ፈፅመዋል የተባሉት ፖሊሶች የአይን እማኞች በመቅረባቸዉ፤ ሁለቱ ፖሊሶች ትናንት ሰኞ ለምርመራ ፍርድ ቤት ቀርበዉ፤ የምርመራዉ ሂደት ለሃሙስ በተለዋጭ ቀጠሮ መተላለፉ ተዘግቦአል። ለፍርድ ቤት የቀረበዉ መረጃ የሁለቱን የኦብነግ መልክተኞች አህመድና ሁሴይን ታፍነዉ ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸዉን ያመላክታል ይላል የፈረንሳይ የዜና ወኪል ያወጣዉ ዘገባ። የኬንያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ሲፖራ ኢንቦሮኪ ዛሬ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት፤ አፈናዉን አከናወኑ የተባሉት ተጠርጣሪዎች በምርመራ ላይ ናቸዉ።

« በዚህ ጉዳይ ላይ ልናገር የምችለዉ፤ ሰዎቹ ተይዘዉ ለምርመራ ተወስደዋል የምርመራዉ ሂደቱም ቀጥሎአል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ፤ መናገር ልሰጥ የምችለዉ መረጃ ይህን ብቻ ነዉ »

ቃል አቀባይዋ የበለጠ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ በተደጋጋሚ ገልጸዉልናል። ናይሮቢ ላይ ታፈነዉ ተወስደዋል የተባሉት ሁለቱ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ ኦብነግ ዋና ተደራዳሪ፤ ባለስልጣናቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለድርድር ናይሮቢ ላይ ለመገናኘት የመጡ መሆናቸዉን በለንደን የሚገኙት የድርጅቱ የተደራዳሪዎቹ ዋና ተጠሪ አብዲ ረመዳን ማሃዲ መናገራቸዉን ዘገባዉ አያያዞ ይጠቁማል። የኦብነግ ተደራዳሪዉ በስልክ ለዜና ወኪሉ እንደገለጹት ሁለቱ ተጠላፊዎች ባልታወቁ ሰዎች ለምሳ ተጋብዘዉ፤ ከምግብ ቤት ሲወጡ ነዉ ታፍነዉ የተወሰዱት። ከዝያም በመኪና እስከ ኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር ሞያሌ ተወስደዉ ከሞያሌ በሄሌኮፕተር እንዲሳፈሩ ተደርጎአል።

Nairobi Skyline Kenia Stadtansicht
ምስል Getachew Tedla

በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸዉ ማንም የተጠለፈ የለም፤ የሶማልያ ክልል መንግስትም ሰዎቹ ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መምጣታቸዉን ነዉ፤ ያስታወቁት ብለዋል።

ሁለት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ «ኦብነግ» አባላትን ናይሮቢ ላይ አፍነዉ ወስደዋል ተብለዉ የአይን እማኝ የቀረበባቸዉ፤ ሁለት የኬንያ ተጠርጣሪ ፖሊሶች፤ ትናንት ለምርመራ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ጉዳያቸዉ በተለዋጭ ቀጠሮ ከነገ በስትያ ሃሙስ እንደሚታይ ተመልክቶአል።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ