1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ

ሐሙስ፣ ሰኔ 9 2008

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት በነሀብታሙ ሚልኬሳ መዝገብ በፀረ ሽብር ሕግ የተከሰሱ 33 ሰዎች ጉዳይን ሲያደምጥ ዋለ ።

https://p.dw.com/p/1J8GS
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

[No title]


ተከሳሾች ቄሮ ቢሊሱማ በሚል የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር፣ ኦነግ የወጣቶች ክንፍ ስር በመደራጀት የኦነግን ተልዕኮ እና ዓላማን ለመፈፀም በሚያስችላቸው አደረጃጀት ተጠቅመው በፀረ ሽብር ተግባር ተሰማርተዋል በሚል ነው ክስ የተመሰረተባቸው። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ዓቃቤ ሕግ መልስ እንዲሰጥ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ውሎውን አብቅቶዋል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ