1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከሰሩ ባንኮችን መንግስት የመጠቅለሉ ሂደት በጀርመን

ሐሙስ፣ የካቲት 12 2001

የጀርመን ካቢኔ ክስረት የደረሰባቸዉን የግል ባንኮች ወደመንግስት የመጠቅለል እቅድ ትናንት አጸደቀ። የዚህ ዓይነቱ ርምጃ በመጀመሪያ ተግባራዊ የሚሆነዉም ለግንባታ ብድር በሚሰጠዉና የፋይናንስ ቀዉሱን ተከትሎ ክስረት ባሽመደመደዉ ሂፖ ሪል ኤስቴት / HRE /በተሰኘዉ ተቋም ይሆናል።

https://p.dw.com/p/Gxc8
...HRE በቀይ መብራት ...
...HRE በቀይ መብራት ...ምስል picture alliance/dpa

ቀደም ሲል ባንኩ የደረሰበትን ክስረት ያጤነዉ የጀርመን መንግስት ለድርጅቱ ከ80 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ቢሰጥም መሻሻል አላሳየም። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ በጀርመን የግል ዘርፉን የመንከባከቡን ሂደት ይፃረራል በተባለዉ በዚህ ህግ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ በርክተዋል።

sl