1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከሸፈው የመንግስት እና የኦብነግ ቅድመ ድርድር

ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2005

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና የኢትዮጵያ መንግስት ለቅድመ ድርድር ከተስማሙ በኋላ በኬንያ ያደረጉት ሁለተኛ ዙር ቅድመ ድርድር መክሸፉን ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/16TPC
ምስል picture-alliance/dpa

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና የኢትዮጵያ መንግስት ለቅድመ ድርድር ከተስማሙ በኋላ በኬንያ ያደረጉት ሁለተኛ ዙር ቅድመ ድርድር መክሸፉን ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶይቸ ቬለ፣ ድርድሩ የከሸፈው ኦብነግ ህገ መንግስቱን ስለማያከብር እና በህገ መንግስቱ ማዕቀፍ መሠረት የመሥራቱን ነገር ስላልተቀበለው ነው ብለዋል።

ኦብነግን በመወከል ናይሮቢ ለቅድመ ድርድሩ የተገኙትን የግንባሩን የዉጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂን የሎንዶኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ አነጋግሯቸዋል፤ ስምምነቱ ሊፈርስ የቻለበትን ምክናንያት ገልፀዋል፤

ልደት አበበ

ድልነሳ ጌታነህ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ