1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከንባታ ሕዝብ የአደባባይ ሠልፍ

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2007

ዱራሜ ከተማ ዛሬ በተደረገዉ ሠልፍ የተካፈሉ እንደሚሉት በአካባቢዉ የመኪና መንገድ፤ዩኒቨርስቲ እና መሠል የመሠረተ-ልማት አዉታሮች እንዲዘረጉ ሕዝቡ በተደጋጋሚ ላቀረበዉ ጥያቄ የአካባቢዉ መስተዳድም ሆነ ፌደራላዊ መንግሥት ተገቢዉን መልስ አልሰጡም።

https://p.dw.com/p/1EZ7X

የከንባታ ሕዝብ በብዛት የሚኖርበት አካባቢ የመሠረተ-ልማት አዉታሮች ተነፍጎታል በማለት ዛሬ ቅሬታዉን በአደባባይ ሠልፍ ጠየቀ።በደቡብ ኢትዮጵያ መስታዳድር ዱራሜ ከተማ ዛሬ በተደረገዉ ሠልፍ የተካፈሉ እንደሚሉት በአካባቢዉ የመኪና መንገድ፤ዩኒቨርስቲ እና መሠል የመሠረተ-ልማት አዉታሮች እንዲዘረጉ ሕዝቡ በተደጋጋሚ ላቀረበዉ ጥያቄ የአካባቢዉ መስተዳድም ሆነ ፌደራላዊ መንግሥት ተገቢዉን መልስ አልሰጡም።«ልማት ተነፈግን» የሚለዉ ሠልፈኛ ፤የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሌሎች አካባቢዎች ሁሉ ለዱራሜ ከተማም ሆነ ለአላባ ጠንባሮ አካባቢ ተገቢዉን የመሠረተ-ልማት አዉታር መንፈግ የለበትም ባይ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝርዝር አገባ አለዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ