1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኩላሊት ህመምተኞች ፈተና

ዓርብ፣ መስከረም 7 2008

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት በዘውዲቲ ሆስፒታል ሊያስገነባ ላቀደው የህክምና ማዕከል ገንዘብ እያሰባሰበ ነዉ። በሳምንት ለአንድ ሰዉ እስከ 5 ሺህ ብር ወጪ የሚጠይቀው የኩላሊት እጥበት ለበርካታ ህሙማን ከባድ ፈተና እንደሆነ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1GYT3
Symbolbild Menschliche Niere Grafik
ምስል Colourbox



አሁን የፅኑ ኩላሊት እጥበት (ሆሞዴያሊሲስ) ማዕከል ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ማህበር 43 መስራቾች መካከል በህይወት ያሉት አንዱ ብቻ ናቸው።

ይህ ባለፈው የካቲት ወር ለእይታ የበቃ ላምባ የተሰኘ የአማርኛ ፊልም ነው።በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ፊልም በኩላሊት ህመም የምትሰቃይ ወጣት ቤተሰብን ውጣ ውረድ ይተርካል። ወጣቷ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለማሳከም ቤተሰቧ ያለውን ሁሉ ይሸጣል። የቤተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ የሚተርከው ላምባ ደራሲና ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ኃይሌ ናቸው።
ላምባ ለእይታ ቀርቦ ከሚገኘው ገቢ በዘውዲቱ ሆስፒታል ለሚገነባው የኩላሊት ህክምና ማዕከል ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አልተሳካም። ፊልሙ ተሰርቆ በኢንተርኔት በነጻ ለእይታ መቅረቡ ከታሰበለት ዓላማ አስተጓጉሎታል። የኩላሊት ህመም ላለባቸው እና አፋጣኝ ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ችግሩ ውስብስብ ነው።
የፊልም ባለሙያው አቶ አንተነህ ኃይሌ የመጀመሪያው ሙከራቸው ቢከሽፍም እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም። አቶ አንተነህ ከጥቂት አመታት በፊት በተመሰረተው የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አባል ናቸው። ማህበሩ ሲመሰረት 43 አባላት የነበሩት ቢሆንም 42ቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኢትዮጵያ በቂ የኩላሊት ህክምና ማዕከላት የሏትም። በዓለም የጤና ድርጅት ባለፈው ዓመት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የኩላሊት ህመም በዓመት ለ7,528 ሰዎች ሞት ምክንያት ነው ።ይህ ኢትዮጵያን ከዓለም በ77ኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል። በህመሙ ላይ በቂ መረጃ አለመኖር፤አነስተኛ ግንዛቤ እና በዘርፉ የሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን የኩላሊት ህመምና ህክምና ያሉበት ችግሮች ናቸው።
አቶ አንተነህና በአባልነት የሚንቀሳቀሱበት የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት በአዲስ አበባ ዘውዲቱ ሆስፒታል የፅኑ ኩላሊት እጥበት (ሆሞዴያሊሲስ) ማዕከል ለማቋቋም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ማህበሩ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ህንጻን በማደስ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉንና አቶ አንተነህ ተናግረዋል።

የላምባ ፊልም ሲጠናቀቅ በኩላሊት ህመም የምትሰቃየው ወጣት ህይወቷ ያልፋል። የወጣቷ ሞት ከሐዘንና ሰቆቃ ይልቅ ለዘላቂ መፍትሄ የመንቃት መልዕክት ያስተላልፋል። በትወናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ደግሞ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅትን ህልም ለማሳካት በቀዳሚነት አስተዋጽዖ እያበረከቱ ነው።

25.06.2014 DW fit und gesund Niere
ምስል Fotolia
16.07.2015 Fit und Gesund Niere


እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ