1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካቤኔ ሹምሽርና አንድምታዉ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 24 2009

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደስአለኝ ከትናንት ወድያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቁት አዲስ ካቢኔ ሰዎችን ከመቀያየር ባለፈ ጠቀሜታ የለዉም ሲሉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/2S73N
Äthiopien Neubildung Kabinett
ምስል DW/Y. Gebergziabeher

Eth,cabinet Reshuffling - MP3-Stereo

 በኢትዮጰያ ኢየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃዉሞ ተከትሎ ጠ ቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ  የፌደራል መንግስቱን  ካቢኔ እንደ  እንደ አዲስ  ማዋቀር  መንግስት ለሚያደ ርገዉ  ተሃድሶ  አንድ አካል  እንደሚሆን  ከወራት በፊት ተናግረዉ ነበር ፣  በ አዲስ  መልክ ያዋቀሩት ካቢኔ  የሀገሪቱ  የህዝብ  ተወካዮች ምክር ቤት  ከተናነት ወዲያ አጽድቆታል።አዲስ የተዋቀረዉ ካቢኔ መልካም አስተዳደር ን  ለማስፈንና   ሙስናን በመዋጋት  ረገድ ተስፋ የተጣለበትና ለዉጥ የሚያመጣ መሆኑን  መንግስት እየገለጸ  ቢሆንም መሰረታዊዉን  የህዘብ ጥያቄ  ከመመለስ አንጻር ግን  የሚያመጣዉ ለዉጥ ሊኖር አይችልም  በሚል በአንዳንዶች ዘንድ  እየተተቸ ይገኛል ።ጉዳዩን  በተመለከተ  ያነጋገርናቸዉ ስማቸዉ  እንዳይጠቀስ  የፈለጉ አንድ የአማራ ከክልል  ነዋሪ እንደሚሉት  ግን  የአዲሱ ካቢኔ አባላት ሙሉ  በሙሉ  የህብረተሰቡን  ጥያቄ ባይመልሱም  ህዝቡ  ጥያቄ  እያነሳ ባለበት ወቅት  የተ ሾሙ  በመሆናችዉ  መልካም አስተዳደርን በማስፈን  ረገድ   በተወሰነ  መልኩም  ቢሆን  የተሻለ ስራ  ሊሰ ሩ ይችላሉ የሚል ተስፋ አላቸዉ።ዶክተር ዳንኤል ተፈራ በዩኤስ አሜሪካ ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉት የምጣኔ ኃብት ባለሞያ ናቸዉ። እሳቸዉ እንደሚሉት የመታደስ ጅማሮ ሹመኞችን በመቀያየር ሳይሆን ሕዝቡ ያነሳዉን መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚመልስስ መሆን አለበት። እንደ ዶክተሩ ገለፃ ሕዝቡ ያነሳቸዉን ጥያቄዎች ለመመለስ መንግሥት በመጀመርያ ጥያቄዎቹን በሚገባ መገንዘብና ማየት አለበት ። ከችግሮቹ ዉስጥ አንዱ የሆነዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ብቻ ለመመለስ በሞመሞከር እንደ መሪት ባለቤትነት የመሰሉትን ጥያቄዎች እና ሌሎቹን መሠረታዊ ጉዳዮች መመለስ አይቻልም ሲሉ ይናገራሉ። መንግሥት ከፓርቲ መዋቅር ወጥቶ ግለሰቦችን ያሳተፈበት ፤ ከብሔር ተዋጽኦ አንጻርም የተሻለና ለትምህርትና  ለሞያ ብቃት ቦታ የሰጠ ነዉ የተባለዉን አዲሱን የካቢኔ አዋቃቀር በተመለከተ አስተያየቱን የሰጠን ነዋሪነቱ ሆላንድ ሃገር የሆነ ወጣት ፖለቲከኛ አቶ ገረሱ ቱፋ ይባላል። አቶ ገረሱ እንደሚለዉ ከሆነ ጤናማ አሰራር በሌለበትና ከሕዝብ ጋር ግጭት ዉስጥ በተገባበት ሁኔታ የትምህርት ዝግጅት ብቻዉን  ጠቀሜታ የለዉም ባይ ነዉ። አቶ ገረሡ አያይዞም መንግሥት ሰዎችን ከመቀያየር ባለፈ መሠረታዊ ለዉጥ ላይ ማተኮር እንዳለበት ይገልፃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደስአለኝ ከትናንት ወድያ ይፋ ካደረጉት 30 የካቢኔ አባላት ውስጥ  21 አዳዲስ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ነባር ሚኒስትሮች ናቸው  ሁለቱ  የዶክትሪት ዲግሪ ያላቸዉ፤ ሁለቱ የፕሮፊሰርነት ቀሪዎቹ ደግሞ የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸዉ መሆናቸዉ ተገልጿል።   

Äthiopien Neubildung Kabinett
ምስል DW/Y. Gebergziabeher
Äthiopien Neubildung Kabinett
ምስል DW/Y. Gebergziabeher

ፀሐይ ጫኔ 

አዜብ ታደሰ