1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካታሎንያ ሕዝበ-ውሳኔ ውዝግብ 

ሰኞ፣ መስከረም 22 2010

በካታሎንያ የስፔን ራስ ገዝ ግዛት ትናንት ተጠርቶ የነበረው ሕዝበ-ውሳኔ ሕዝብ እና ፖሊስን አጋጭቶ በርካቶችንም ለቁስለኝነት ዳርጎ ድብልቅ ስሜትም ፈጥሮ አልፏል። ግዛቲቱን ከስፔን ለመገንጠል የሚጠይቀው ይኸ ሕዝበ-ውሳኔ በማዕከላዊው መንግሥት በሕገ ወጥነት ተፈርጆዋል።

https://p.dw.com/p/2l7au
Spanien Barcelona Referendum über Unabhängigkeit - Polizeieinsatz in Barcelona
ምስል picture alliance/AP/M. Fernandez

ካታሎንያ

በዚህም የተነሳ እንዳይደረግ ትዕዛዝ ተላልፎበት የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ ባለሥልጣኖች ግን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አሻፈረኝ በማለት ወደ ምርጫ በመግባታቸው ከስፔን ፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። እንመርጣለን በሚሉት ካታሎናውያን እና አትመርጡም በሚሉት የስፔን ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ800 በላይ ሰላማዊ ሰዎች እና 12 ፖሊሶች ቆስለዋል። 


ገበያው ንጉሴ 
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ