1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ቴሌቪዥን ያቀረበው ዘጋቢ ፊልም መንግስት ማስከፋቱ

ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2001

በኦሮሞ ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር በኦነግ የዕለት ተዕለት ዕንቅስቃሴ ላይ ያተኮረውና በኬንያ የኔሽን ቴሌቪዥን ጣቢያ የተላለፈው ዘጋቢ ፊልም እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጉን አንድ የኬንያ ጋዜጣ ባለፈው ሰሞን ዘግቧል ።

https://p.dw.com/p/JBXW

የቴሌቩዥን ጣቢያው ከዘጋቢ ፊልሙ ሁለቱን ክፍል ካስተላለፈ በኃላ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጣቢያው ዘገባውን ማስተላለፉን እንዲያቆም ሙከራ ማድረጋቸውን ኔሽን የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል ። የኢትዮጵያ መንግስት ፣ ዘጋቢ ሪፖርቱ መሰረት የሌለው ፕሮፖጋንዳ የሚነዛ ነው ሲል ነው የሚከሰው ። የዓለም ዓቀፍ የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ ድርጅት CPJ በበኩሉ ይህ ተግባር መንግስት ስልጣኑን ላለማጣት ሁሉንም አማራጭ እንደሚጠቀም አመልካች ነው ሲል ወቅሷል ።

አበበ ፈለቀ/ ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ