1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የማጓጓዣ ፕሮጀክት

ዓርብ፣ የካቲት 23 2004

በ 16 ቢልዮን ዶላር ምናልባትም በአጠቃላይ ከ 22 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጅ የማጓጓዣ ፕሮጀክት ለመጀመር ተነሣሥተዋል። ላሙ፤ ኬንያ ላይ የሚደራጀው ወደብ ከ 3,5 ቢሊዮን ዶላር---

https://p.dw.com/p/14Cog
An oil worker turns a spigot at an oil processing facility in Palouge oil field in Upper Nile state February 21, 2012, following a dispute with Sudan over transit fees. South Sudan will refuse do to any business in the future with oil trader Trafigura if it is proven that the firm bought oil from neighbouring Sudan in the knowledge that the cargo was seized southern crude, its oil minister told Reuters. Picture taken February 21, 2012. REUTERS/Hereward Holland (SOUTH SUDAN - Tags: ENERGY POLITICS BUSINESS)
የድቡብ ሱዳን ነዳጅምስል Reuters



ኢትዮጵያንና ደቡብ ሱዳንን ከኬንያ ጋ የሚያገናኝ የባቡር ሀዲድ፤ አውራ ጎዳናና  የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያ ቧንቧ ዝርጋታ ፕሮጀክትን የተመለከተ ልዩ ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ናይሮቢ ውስጥ ከመካሄዱ በፊት ፣ የኢትዮጵያና የኬንያ መሪዎች በዛሬው ዕለት በዚያው በናይሮቢ  በሁለቱ አገሮች መካካል የሚደረጉ የትብብር ውሎችን ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ---ተክሌ የኋላ--
ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን በአያሌ የመሠረተ ልማት ፣ በተለይም የመጓጓዣ መስመሮች የሚያገናኙአቸውን  ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለማካሄድ ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። የባቡር ሀዲድ፣ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ፣ አውራ ጎዳናዎች 3 የአኤሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች  አዲስ የመስተናጋጃ ወደብ ለመስራትና የነዳጅ ዘይት ማጠሪያ አውታር ለመትከል፣ በ 16 ቢልዮን ዶላር ምናልባትም በአጠቃላይ ከ 22 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጅ የማጓጓዣ ፕሮጀክት ለመጀመር ተነሣሥተዋል።
ላሙ፤ ኬንያ ላይ የሚደራጀው ወደብ ከ 3,5 ቢሊዮን ዶላር የማያንስ ገንዘብ የሚፈጅ ሲሆን፣ ከላሙ እስከ ጁባ 1720 ኪሎሜትር የባቡር ሐዲድ በ 7,1 ቢሊዮን ዶላር፣ በሚመጡት 3 ዓመታት ውስጥ ይዘረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የታቀደው ዐቢይ ፕሮጀክት የተጠነሰሰው እ ጎ አ በ 1975 ዓ ም ቢሆንም፣ እንደገና አንሠራርቶ አሁን ተግባራዊ ይሆን ዘንድ እቅዱን ማንቀሳቀስ  የተጀመረው ፣ኬንያ፣ ራእይ 2030 ባላችው ዓላማ ነው። እጅግ በዛ ያለ ገንዘብ የሚጠይቀው ፕሮዠ ተግባራዊ የሚሆንበት ዕድል እስከምን ድረስ ይሆን? በናይሮቢ ፤ ኬንያ የስልታዊጥናቶች ተቋም ከፍተኛ  ተመራማሪ ኢማኑኤል ኪሲያንጋኒ--
«የፕሮጀክቱ የአስፈላጊነት ሁኔታ ሲመረመር፤ እንደሚመስለኝ፣ ጭብጥነት ያለው ነው ከባህር በር ጋር የሚያገናኛትን መሥመር የምትሻ አዲስ ሀገር ተፈጥራለች ፤- ደቡብ ሱዳን !ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ችግር ያለባት እንደመሆኗ መጠን ፣ ይህን ሰፊ ፕሮጀክት መዘርጋቱ ተገቢ ይሆናል። የኬንያ መንግሥትና ተባባሪዎቹ፣ ፕሮጀክቱን በሚገባ ለማካሄድ ይቻላቸዋል?አይቻላቸውም? ጊዜ ጠብቆ ማየቱ ሳይሻል አይቀርም።»
በ 3ቱ  አገሮች መካከል እንዲከናወኑ  የታቀዱት ፕሮጀክቶች በመሠረተ-ልማትም ሆነ በኤኮኖሚ ግንባታና በመሳሰለው ጠቃሚነታቸው ባያጠራጥርም፣ በተፈጥሩ አካባቢ ጥበቃ ላይ ያተኮሩ ወገኖች ቅሬታ አላቸው።
«አዎ አሳሳቢነቱ አለ። ይሁን እንጂ እንደኛ ግንዛቤ የኬንያ መንግሥት የተፈጥሮ አካባቢ ይዞታን መመርመሩ አልቀረም። በአመዛኙ አሳሳቢነቱን የሚገልጹት የአካባቢ ማኅበረሰብ አባላት ናቸው። ለምን? ይኸው ፕሮጀክት ያፈናቅለናል ብለው ስለሚያሳቡ ነው። ከፕሮጀክቶቱ ጠቀሜታ እንደማያገኙም ነው የሚገልጹት።»
ፕሮጀክቱ፣ ከንግድና ልማት ባሻገር በፀጥታ ረገድ፣ ምን ዓይነት ድርሻ ያበረክታል?
«እንደማስበው ይህ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ኬንያ በአሁኑ ጊዜ ሶማልያ ውስጥ ጦር ጣልቃ ያስገባች በዚህ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። ኬንያ ወደ ሶማልያ ጦር ያዘመተች የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋ ሥጋት ላይ ስለወደቀ ነው የሚሉ አሉ። ነገር ግን እውነተኛው ምክንያት፣ ታማኝ ዜና ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከአዲሱ ወደብ ጋር የተያያዘ ነው። ወደቡ፤ ከሶማልያና ኬንያ ወሰን 60 ኪሎሜትር ገደማ ነው የሚርቀው። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ፣ ባቡር ሐዲድና የመሳሰሉት ሊዘረጉ የታቀዱት ከሶማልያና ፀጥታው እምብዛም የተረጋጋ እንዳልሆነ ከሚነገርለት ከደቡባዊው  ኢትዮጵያ የሚርቅ አይደለም። እንደታማኝ ዜና ምንጮች  አገላለጽ ፤ ኬንያ ፤ ሶማልያ ውስጥ ጦር ያስገባችው  ደቡባዊውን ሶማልያ በማረጋጋት ፣ ለራሷ የኤኮኖሚ ጥቅም በማሰላሰል ነው።»

ተክሌ የኃላ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ