1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ዕቅድ እና ስደተኞች

ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008

ኬንያ ሁለት ትላላቅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎቿን እንደምትዘጋ እና ከአሁን በኋላም የሶማሊያ ስደተኞች እንደማትቀበል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታውቃለች ።

https://p.dw.com/p/1IkNp
Kenia Das Flüchtlingslager Dadaab
ምስል picture alliance/dpa/UNHCR/B. Bannon

[No title]

ስደተኞችን ከሚረዱ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ይሠራ የነበረውን የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት መዘጋቱንም መንግሥት አስታውቋል ። መንግሥት ለመዝጋት ያቀደው 328 ሺህ ስደተኞች የተጠለሉበትን የዳዳብ እንዲሁም 190 ሺህ ስደተኞች ያሉበትን የከካኩማ የስደተኞች መጠለያዎችን ነው ።ዳዳብ ከሚገኙት ስደተኞች አብዛኛዎቹ ሶማሌዎች ሲሆኑ ካኩማ ካሉት የሚያመዝኑት ደግሞ ደቡብ ሱዳናውያን ናቸው ። ኬንያ መጠለያዎቹ የአሸባሪዎች መፈልፈያ ሆነዋል ስትል ትከራከራለች ። የኬንያን እቅድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አውግዘዋል ።ስለ ኬንያ እቅድ እና ስለ ተነሳበት ተቃውሞ የናይሮቢውን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ