1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ፖለቲከኞች ዉዝግብ

ሐሙስ፣ መስከረም 18 2010

የፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ የጁቢሊ ፓርቲ እና በራይላ ኦዲንጋ የሚመራዉ ናሳ የተባለዉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተወካዮች ዛሬ ሥለምርጫ ለመነጋገር ቢሰሰበሰቡ ስብሰባዉ ባፍታ ተበትኗል

https://p.dw.com/p/2kuch
James Orengo und andere Repräsentanten der  NASA Koalition in Kenia
ምስል DW/T.Maruko

(Q&A) Kenia-Regierung und oppositionen Streit - MP3-Stereo

የኬንያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች በመጪዉ ጥቅምት አጋማሽ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ዛሬም አልሰከነም።የፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ የጁቢሊ ፓርቲ እና በራይላ ኦዲንጋ የሚመራዉ ናሳ የተባለዉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተወካዮች ዛሬ ሥለምርጫ ለመነጋገር ቢሰሰበሰቡ ስብሰባዉ ባፍታ ተበትኗል።የገዢዉ ፓርቲ የሚበዛበት የሐገሪቱ ምክር ቤት በበኩሉ የሐገሪቱን የምርጫ ሕግ ለመቀየር አዳዲስ ማሻሻዎችን አቅርቧል።የተቃዋሚዉ ፓርቲ የምክር ቤት እንደራሴዎች ማሻሻያዉን በመቃወም የምክር ቤቱን ሥብሰባ ረግጠዉ ወጥተዋል።የናይሮቢ ተባባሪ ዘጋቢያችን ፍቅረ-ማርያም መኮንንን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ፍቅረ-ማርያም መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ