1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የክብር ዶክተር አበበች ጎበና እና ሥራዎቻቸው

እሑድ፣ ጥቅምት 14 2008

ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል።

https://p.dw.com/p/1Gu27
Abebech Gobena Äthiopien
ምስል DW/Y. Geberegeziabeher

የክብር ዶክተር አበበች ጎበና እና ሥራዎቻቸው

ሕፃኗን ከሌላ አንዲት ሕፃን ጋር ይዘውም ለማሳደግ ይወስዳሉ። እናም ወዲያው 21 ሕፃናትን ለመርዳት ያሰባስባሉ። ሆኖም ባለቤታቸው እና የሥራ አለቃቸው ከሕፃናቱ ወይ ከእኔ አለያም ከሥራዎ የሚል ከባድ አጣብቂን ውስጥ ይከቷቸዋል። ሆኖም እሳቸው ለሕፃናቱ ይወስናሉ። በአሁኑ ወቅት ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ከ12 ሺህ በላይ ሕፃናትን ይረዳሉ። በእሳቸው የርዳታ ድርጅት ሥር ከ1,5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል። በሰብአዊ ርዳታ ለጋሽ ድርጅታቸው 265 ቋሚ እንዲሁም 400 ሌሎች ሠራተኞችን ቀጥረው

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ