1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ህልፈት

ማክሰኞ፣ መስከረም 10 2009

ለታዋቂዉ ደቡብ አፍሪቃዊ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወታደራዊ ስልጠናን የሰጡት ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ በ80 ዓመታቸዉ ባለፈዉ ሳምንት አርብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

https://p.dw.com/p/1K5Vp
Berliner Mauer Vicor Landeta, Mauerbilder von Friedensnobelpreisträgern
ምስል Elmar Prost, Baustoffe Klösters

[No title]


የኔልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሥልጠና “እጅግ ምሥጢራዊ ነበር” ሲሉ መናገራቸዉን ኔልሰን ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ኮሎኔል ፈቃዱን ዋኬኔን በመጥቀስ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዉላቸዋል ። የዝያን ጊዜዉ የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ የ«ANC» የትጥቅ ትግል ክንፍ አዛዥ ሆነዉ ለስብሰባ ከዚያም ለስልጠና ወደ አዲስ አበባ የመጡት ኔልሰን ማንዴላ፤ በእስራኤል ሃገር በዉትድርና ትምህርት በሰለጠኑት በዚያን ጊዜዉ መቶ አለቃ ፈቃዱ ዋኬኔ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአራት ሳምንታት ወታደራዊ ስልጠናን አግኝተዋል። ስለ ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ማንነት የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን በስልክ አጠር ያለ መረጃ ሰጥቶናል።

ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ