1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮፐንሐገኑ ጉባኤና አፍሪቃ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 8 2002

በጉባኤዉ ላይ አፍሪቃን ወክሎ የሚሳተፈዉ ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀዉ አፍሪቃ ያለ ጥፋቷ ለደረሰባት የአየር ብክለት ጉዳትም የመቶ ቢሊዮን ዶላር ካሳ ትጠይቃለች

https://p.dw.com/p/KZEZ
ምስል Simone Schlindwein

በያዝነዉ ወር ማብቂያ ኮፐንሐገን-ዴንማርክ የሚሰየመዉ አለም አቀፍ የአየር ንብረት የመሪዎች ጉባኤ የአለምን የሙቀት ልቀት መጠንን በአስር-አመት ዉስጥ በግማሽ የሚቀንስ ዉሳኔ እንዲያሳልፍ አፍሪቃ ጠየቀች።በጉባኤዉ ላይ አፍሪቃን ወክሎ የሚሳተፈዉ ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀዉ አፍሪቃ ያለ ጥፋቷ ለደረሰባት የአየር ብክለት ጉዳትም የመቶ ቢሊዮን ዶላር ካሳ ትጠይቃለች።አፍሪቃን የሚወክሉት የአስር ሐገራት መሪዎችና ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተሰብስበዉ የመጨረሻ ባሏቸዉ ሐሳቦች ላይ መክረዋል።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝሩን ልኮል ናል።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ