1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መምህራን ለቤት መስሪያ የተሰጣቸው መሬት ተወስዶብናል ብለዋል

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010

በወላይታ ሶዶ የሚገኙ መምህራን ለቤት መስሪያ የተሰጣቸው መሬት እንደተወሰደባቸው አስታወቁ። ከእነሱ የተወሰደው መሬት ለሌሎች ተሰጥቷል ሲሉ ያማረሩት በ25 ማህበራት የታቀፉት እነኚህ መምህራን ናቸው።

https://p.dw.com/p/2mQoB
Global Media Forum KLICK! 2012 Horst Frommont
ምስል Horst Frommont

መምህራን ለቤት መስሪያ የተሰጣቸው መሬት ተወስዶብናል ብለዋል

በደቡብ ክልል ወላይታ የሚገኙት መምህራን ለግንባታው ከሚያስፈልገው ወጪ 10 ከመቶ ቆጥበው የመሬት ካርታ አግኝተው የነበረ ቢሆንም መሬቱ በጥቅማ ጥቅም ለተሳሰሩ ለሌሎች እንዲሰጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡ የወላይታ ሶዶ ማዘጋጃ ቤት በበኩሉ “ይህን ድርጊት ፈጽሟል ያለውን መሀንዲስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ለመምህራኑ ችግር መፍትሔ መስጠቱን ገልጿል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር የሚመለከታቸውን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል፡፡  

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር    
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ