1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ እና የከንቲባው ምላሽ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2007

በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አካባቢ አርሶአደሮች ያለ አግባብ ከይዞታችን ተፈናቅለናል ሲሉ ማማረራቸውን አንድ የዓይን ምስክር ተናገሩ ። ከተማይቱን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ በሺህዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ እና አርሶአደሮቹም ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ እንደሆነ ለዶቼቬለ አስረድተዋል ።

https://p.dw.com/p/1GROA
Kenia - Eine Frau auf dem Maisfeld
ምስል CC-BY-SA-cimmyt

[No title]

እርምጃው የማረራቸው አርሶ አደሮች ከከተማው መስተዳድር ለችግራቸው መፍትሄ እንዳላገኙ ም የዓይን ምስክሩ ተናግረዋል ።
የአይን ምስክሩ ለስራ ጉዳይ ወደ ወላይታ ሶዶ በሄዱበት አጋጣሚ አየሁ እንዳሉት በወላይታ ሶዶ ከተማ መስፋፋት ሰበብ ቤቶች የፈረሱትና አርሶ አደሮችም ከይዞታቸው የተፈናቀሉት በ8 የገበሪ ቀበሌማህበራት ነው ።
በነዚህ የገበሬ ቀበሌ ማህበራት ከሁለት ሳምንት በፊት በተጀመረው በዚሁ ዘመቻ የፈረ ሱት ከዓመታት በፊት እንዲሁም በቅርቡ ሃላፊዎች በፈቀዱት መሠረት ጭምር ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶች ናቸው ።
የዓይን ምስክሩ እንዳሉት ከነሐሴ አጋማሽ አንስቶ በቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ከ2500 በላይ ሰዎች መኖሪያ የነበሩ ቤቶች እንዲነሱ ተደርጓል ።በዚህ የተነሳም ብዙዎች መግቢያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው እንደ ዓይን ምስክሩ ።
ለከተማው መስተዳደር ሮሮአቸውን ያሰሙት ከይዞታቸው የተነሱት የወላይታ ሶዶ አካባቢ አርሶ አደሮች ለችግራቸውም ሆነ ለስጋታቸው መፍትሄ የሚሆን መልስ አላገኙም ። በዚህ የወላይታ ሶዶ አርሶአደሮች ሮሮ ላይ ከንቲባው ምላሽ ሰጥተውናል።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ