1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልዲያ ሙስሊሞች ተቃዉሞ

ዓርብ፣ ሰኔ 21 2005

በተቃዉሞ የተሳተፉ የከተማይቱ ነዋሪዎች እንዳስታወቁት ፖሊስ መስጊዱን ቢከብም ሠላማዊ ተቃዉሞዉ በሠላም ተጠናቅቋል።ባለፈዉ ሳምንት ታስረዉ የነበሩ ሰወስት የከተማይቱ ነዋሪዎች መለቀቃቸዉንም---

https://p.dw.com/p/18yFE
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የወልዲያ ከተማ (ሠሜን ወሎ) ሙስሊሞች የኢትዮጵያ መንግሥት በሐይማኖታቸዉ ጣልቃ መግባቱን በመቃወም የጀመሩትን ዉግዘት ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ።በከተማይቱ ትልቅ መስጊድ ለጁመዓ ሦላት የታደመዉ ምዕመን መንግሥት መሪዎቹን ማሠሩን፥ መንፈሳዊ ትምሕር ቤቶችን፥ ፅሕፈት ቤቶችን መዝጋቱን፥ እና አሕባሽ የተባለዉን ሐራጥቃ በሐይል መጫኑን በተለያዩ መፈክሮች አዉግዟል። በተቃዉሞ የተሳተፉ የከተማይቱ ነዋሪዎች እንዳስታወቁት ፖሊስ መስጊዱን ቢከብም ሠላማዊ ተቃዉሞዉ በሠላም ተጠናቅቋል።ባለፈዉ ሳምንት ታስረዉ የነበሩ ሰወስት የከተማይቱ ነዋሪዎች መለቀቃቸዉንም የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ያነጋገራቸዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ