1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወሲብ ቅሌት በጀርመን ካቶሊካዊት ትምሕርት ቤቶች

ረቡዕ፣ የካቲት 17 2002

የጀርመን ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን መምሕራንና ቀሳዉስት የቀድሞ ተማሪዎቻቸዉን አስገድደዉ መድፈራቸዉ መጋለጡ የሐገሪቱን የካቶሊክ ምዕመን አሁንም እያነጋገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/MA34
ሊቀ ጳጳስ ሮበርት ሶሊችምስል picture alliance / dpa
ከአንድ መቶ አርባ የሚበልጡ የቀድሞ የካቶሊክ መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች በመምሕሮቻቸዉና በየትምሕር ቤቶቹ ሐላፊዎች መደፈራቸዉን አጋልጠዋል።የጀርመኑ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሮበርት ሶሊች ቀሳዉስቱ ላደረሱት በደል በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።ይቅርታዉ በቂ አይደለም የሚሉ ወገኖች ቤተ-ክርስቲያኒቱ ለተበዳዮቹ ካሳ መክፈል አለባት እያሉ ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ። ይልማ ሐይለ ሚካኤል ,ነጋሽ መሀመድ ሂሩት መለሰ