1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወሲብ ጥቃት ክሶችና ቫቲካን

ዓርብ፣ መጋቢት 17 2002

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አንዳንድ የእምነት አባቶች ፈፅመዋል የሚባለዉን የወሲብ ቅሌት ያጋለጠዉን የ "New York Times" ን ዘገባ ቫቲካን አስተባበለች።

https://p.dw.com/p/MfEj
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛምስል AP

ጋዜጣዉ የአሁኑ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቀ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ የያኔዉ ካርዲናል ዮሴፍ ራትዚንገር በዊስኮንሰን ግዛት በሚላዉኪ አገረ ስብከት ስለተፈፀመዉ የወሲብ ጥቃት መፈፀሙን እያወቁ ሸፋፍነዉ መቆየታቸዉን ያትታል። በተጠቀሰዉ ስፍራ 200፤ በጣሊያን ደግሞ 67 ፅሙማን ልጆች የወሲብ ጥቃቱ ሰለባዎች መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ