1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወዳጅነት ትምሕርት ቤት

ዓርብ፣ ጥቅምት 27 2002

የማሼል-ሆኔክር የሩቅ እቅድ ወጣቶችን በኮሚንዝም ርዕዮት አንፆ ሥርዓቱን የዝንተ-አለም፥ የመላዉ አለም ርዕዮት የማድረግ አይነት ነበር

https://p.dw.com/p/KQIv
ሆኔከርና ባለቤታቸዉምስል AP

የበርሊን ግንብ ከመናዱ በፊት የጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (የምሥራቅ ጀርመን) ፖለቲከኞች ሕልም-አለማ ብዙ፥ ሩቅም አይነት ነበር።ምሥራቅ በርሊኖች እንደ ሞስኮና ሐቫና ብጤዎቻቸዉ ሁሉ ከሚንስታዊዉን ርዕዮተ-አለም በመላዉ አለም ለማስረፅ በየሐገሩ በተለይም ምጣኔ ሐብታዊ ችግር በተጫጫናቸዉ፣ የምዕራቡ ፖለቲካዊ ስርዓት ባማረራቸዉ አፍሪቃን በመሳሰሉት ሐገራት ወጣቶች ልዩ ላይ ትኩረት አድርገዉ ነበር።

በየሥፍራዉ በጣሙን በአፍሪቃ ዉስጥም አባባሪ-ተባባሪ አላጡም።ከአፍሪቃ አንዱ የሞዛምቢክ የመጀመሪያ መሪ ሳሞራ ማሼል አንዱ ነበሩ።የዶቼ ቬለዋ ባልደረባ ማርታ ደ አልማይዳ ባሮሶ እንደ ዘገበችዉ የማሼል-ሆኔክር የሩቅ እቅድ ወጣቶችን በኮሚንዝም ርዕዮት አንፆ ሥርዓቱን የዝንተ-አለም፥ የመላዉ አለም ርዕዮት የማድረግ አይነት ነበር።ባንድ የቀድሞ ትምሕር ቤት ላይ የተመሠረተዉን የባሮሶን ዘገባ ይልማ ሐይለ-ሚካኤል አጠናቅሮታል።

ማርታ ባሮሶ/ ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ