1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣት ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር

ዓርብ፣ ግንቦት 15 2006

«በአገራችን ኢትዮጵያ የደራስያን፤ የሙዚቀኞች ማኅበር ከተቋቋመ እጅግ ረጅም ግዜ ቢሆንም እስከ ዛሬ ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር አቋቁመዉ ልምዶቻቸዉን ሲለዋወጡ ባለማየታችን፤ ይህን ማህበር አቋቋምን» ያለን ወጣት ሰዓሊ የዛሬዉ የወጣቶች ዓለም ዝግጅታችን እንግዳ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1C4oj
Austellung AFRIKA mit eigenen Augen
ምስል Thomas Viering

ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር ከተቋቋመ በኃላ፤ በአዲስ አበባም ሆነ በክፍለ ሀገር የሚገኙ በርካታ ወጣት ሰዓልያን እና ቀራፅያን ልምድ መለዋወጥ መጀመራቸዉ ተነግሮአል። ስለ ሥነ-ጥበባቱ ማህበር እንቅስቃሴ የለቱ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።

የዛሬ ሶስት ዓመት አዲስ አበባ ላይ የተቋቋመዉ ሰዓልያን እና የቀራፅያን ማኅበር፤ በተለይ በርካታ ወጣት የስነ-ጥበብ ሰዎችን ማሰባሰቡ ተነግሮለታል። የማኅበሩ ዋና ፀኃፊ ወጣት ሰዓሊ ሰይፉ አበበ፤ ሰዓሊያን እና ቀራፂያን በማኅበር ባለመሰባሰባቸዉና ልምድ ባለመለዋወጣቸዉ ይህ ማኅበር ሊቋቋም ቻለ ሲል ገልፆልናል።

የሰዓልያን እና የቀራፅያን ማህበሩ ከተቋቋመ በኃላ በዚህ ሶስት ዓመት ዉስጥ በየዓመቱ የሚዘጋጅ አዉደ ርዕይ እንደሚኖርና፤ እስከ ዛሪም በተደረጉ አነስተኛ ዓዉደ-ርዕዮች በርካታ የሥነ-ጥበብ ሥራዎች መሸጥ መቻሉና ወጣቱ የስነ-ጥበብ ፍላጎቱን የሚያሟላበት ቁሳቁስ መግዣ ሟሟያ ሊያገኝ የሚችልበት መንገድ መፈጠሩን ወጣት ሰይፉ ተናግሮአል። ማኅበሩ ሥነ- ጥበብን ለህዝብ ከማስተዋወቅ እና ሰዓሊዉ የሚጠቀምበትን ከማመቻቸት ባሻገር፤ ልምድ መለዋወጫ የዉይይት መድረክ እንዳለም ይገልፃል። ከአንድ ሳምንት በኃላ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዓመታዊ የሥነ-ጥበብ ፊስቲቫል፤ ለማዘጋጀት በሥራ ተጠምዶ እንደሚገኝ የማኅበሩ ዋና ፀኃፊ ወጣት ሰዓሊ ሰይፉ አበበ ገልፆአል። ሰዓሊ ሰይፉ በሥነ-ጥበቡ ረገድ ባለፉት ዓመታት በርካታ ወጣቶች ከፍተኛ ፍላጎትና ድንቅ ሥራ እያሳዩ መምጣታቸዉን ገልፆአል።

Africani in Africa Neue Kunst aus Afrika steht im Mittelpunkt einer großen Ausstellung in Florenz. Die Schau Afrikaner in Afrika vereint über 130 Werke vo
ምስል presse

የዛሪ ሶስት ዓመት ሶስት ወጣት ሰዓሊዎች እና ቀራፅያን ተሰባስበዉ ያቋቋሙት ጥላ ማኅበር ቢኖሩም በአሁኑ የኑሮ አያያዝ የሁሉን ጥረት እንደሚጠይቅ የማኅበሩ ፀሐፊ ሳይገልፅ አላላፈም።

ወጣት የሰዓልያን እና የቀራፅያን ማኅበርአዲስ አበባ በሚያዘጋጀዉ ፊስቲቫል ላይ የሥነ-ጥበብ አፍቃሬዎች ተገኝተዉ አስተያየት እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪዉን አቅርቦአል። ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ መጫዉን በመጫን ያድምጡ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ