1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣት ሥራ አጦች

ዓርብ፣ ነሐሴ 20 2008

ILO በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠረዉ የዓለም የሥራ ድርጅት ሰሞኑን ባወጣዉ ዘገባዉ የአዳጊ ሐገራት ወጣት ሥራ-አጥ ቁጥር በያዝነዉና በመጪዉ የጎርጎሪያኑ ዓመት መጨሩ አይቀርም።

https://p.dw.com/p/1JqHB
ምስል Getty Images/AFP/F. Scoppa

[No title]

የደሐና በማደግ ላይ ያሉ ሐገራት መንግሥታት ለወጣቶቻቸዉ የሥራ ዕድል ካልፈጠሩ የወጣቶች ፍልሰትና ስደት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ እንደማይቀር የዓለም ሥራ ድርጅት አሳሰበ።ILO በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠረዉ የዓለም የሥራ ድርጅት ሰሞኑን ባወጣዉ ዘገባዉ የአዳጊ ሐገራት ወጣት ሥራ-አጥ ቁጥር በያዝነዉና በመጪዉ የጎርጎሪያኑ ዓመት መጨሩ አይቀርም።ድርጅቱ ለወጣት ሥራ አጦች ቁጥር መጨመር ከጠቀሳቸዉ ምክንያቶች አንዱ የብራዚል እና የአርጀንቲና የምጣኔ ሐብት እንቅስቃሴ መዳከም ነዉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ