1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣቶች መድረክ

ዓርብ፣ ኅዳር 8 2004

ባለፈው ሳምንት ጥንቅራችን «በማድመጥ መማር» ተከታታይ የሬዲዮ ድራማችን ላይ ከተሳተፉ ሶስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ቆይታ አድርገን ነበር። የወጣቶች መድረክ ዝግጅታችን የተመደበልን ሰዓት ተገባዶ ክርክሩን ለማቋረጥ ስንገደድ ወጣቶቹ ሞቅ ያለ ክርክር ላይ ነበሩ። እናም ቃል በገባነው መሰረት ሳምንት ካቆምንበት እንቀጥላለን።

https://p.dw.com/p/Rx35
በማድመጥ መማር ለወጣቶቹ...ምስል DW

ኣሶስቱም ወጣቶች የአዲስ አበባ ዩነቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ሊያ አበበ በሲቪል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ናት። መቅደስ ታደሰም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የአምስተኛ ዓመት ትምህርቷን በማገባደድ ላይ ናት። አሚር አማን ደግሞ በጋዜጠኝነት የትምህርት ዘርፍ የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው። አሚር ከዚህ ቀደም የሚከታተለውን የህክምና ሳይንስ ትምህርት በማቋረጥ ነው ወደ ጋዜጠኝነቱ የዞረው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ