1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉቅሮ

ሰኞ፣ ሐምሌ 11 2008

ከአክሱም ዘመነ መንግሥት በፊት የነበረዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ቀስ እያለ በማስረጃ ብቅ ማለት የጀመረ ይመስላል። የዛሬ ስምንት ዓመት ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ዉቅሮ ላይ በተጀመረዉ የቅርሳ ቅርስ ፍለጋ እና ቁፋሮ አንድ ጥንታዊ ቤተ-መንግሥት መገኘቱን በርሊን ላይ በተካሄደ አንድ ስብሰባ ተገልፆአል።

https://p.dw.com/p/1JQyY
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

[No title]

በርሊን በሚገኘዉ ፍሪ ዩንቨርስቲ የከርሰ ምድር ጥናት ተቋም ዉስጥ በተካሄደዉ በዚህ ስብሰባ ላይ እንደተነገረዉ ዉቅሮ ላይ የተገኘዉ ይህ ጥንታዊ ቤተ -መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተገነባ ነዉ ። በኢትዮጵያ ቤተ መዘክሮችን ለማጠናከርና ለማስፋፋት የተቋቋመ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት የዉቅሮን ጥናት አስመልክቶ በርሊን ላይ ያካሄደዉን ስብሰባ የተከታተለዉ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።


ይልማ ኃይለሚካኤል


አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ