1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ የዉጭ ዜጎች ይዉሉልን የሚለዉ ተቃዉሞ አይሏል፤

ዓርብ፣ የካቲት 17 2009

ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የዉጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠረዉ ጥላቻ እና ጥቃት ተባብሶ ቀጥሏል። ፕሪቶሪያ ውስጥ የውጭ ዜጎች ከሀገሪቱ እንዲወጡ በሚጠይቁ ሰልፈኞች እና ሰልፉን በሚቃወሙ  የውጭ ዜጎች መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ ፖሊስ የላስቲክ ጥይቶች መተኮሱ እና ውኃ መርጨቱም ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/2YE7g
Südafrika Straßenszene geschlossene Geschäfte in Joannesburg
ምስል DW/M. Ayele

MMT_Q&A Xenophoic attack in South Africa - MP3-Stereo

ዛሬ ወደ ሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያመራ በነበረው ሰልፍ ላይ ከተካፈሉት አንዳንዶቹ ዱላ ይዘው ነበር። ጥላቻን ያንጸባርቅ የነበረው ይህ ሰልፍ መፈቀድ አልነበረበትም ሲል በኔልሰን ማንዴላ ስም የሚጠራው ድርጅት ወቅሷል።  ሥራ አጥነት ከ25 በመቶ በላይ በሆነበት በደቡብ አፍሪቃ የውጭ ዜጎች የሀገሪውን ሥራ እየወሰዱ ነው የሚሉ ክሶች ተደጋግመው ይቀርባሉ።  በዛሬዉ ዕለትም የዉጭ ዙጎች ከሀገሪቱ ይዉጡ የሚሉ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን ፖሊስ ሰልፉን በመበተን ሥራ ተጠምዶ ተሰምቷል። ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ይዉጡ የሚለዉን ሰልፍ የተቃወመ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚህ መካከልም የዉጭ ዜጎች ንብረቶች የሆኑ በርካታ ሱቆች ተዘግተዉ መዋላቸዉን ጆሃንስበርግ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን መላኩ አየለ ገልጾልናል።

መላኩ አየለ

ሸዋዬ ለገሠ