1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ዜጎች በአውሮፓ

ሐሙስ፣ ሰኔ 11 2001

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ጉባኤ ተቀምጠዋል ። መሪዎቹ በአሁኑ ጉባኤያቸው ትኩረት ሰጥተው ከሚነጋገሩበት ጉዳይ ውስጥ በሚቀጥለው ህዳር የስራ ጊዜያቸው የሚያበቃው የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት የሆሴ ማኑዌል ባሮሶ በድጋሚ ለኮሚሽኑ ፕሬዳንትነት ዕጩ ሆኖ መቅረብ አንዱ ነው ።

https://p.dw.com/p/IUJl
በጀርመን የውጭ ዜጎች ቋንቋ ሲማሩምስል dpa - Bildfunk

ከአባል ሀገራት አንዳንዶቹ የውጭ ዜጎችና የውጭ የዘር ሀረጋቸው ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከሚኖሩበት ሀገር ህዝብና ስርዓት ጋር ምን ያህል ተዋህደው እንደሚኖሩ ቁጥጥርና ክትትል የሚያካሂዱበት አሰራር ዘርግተዋል ።የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተዋህደው የሚኖሩበትን መንገድ ማሻሻል የአባል ሀገራት ፍላጎት ነው ። ይህ የጀርመንም ፍላጎት ነው ። ታዲያ ይህ ፍላጎትና ተጨባጩ ሁኔታ በጀርመን ምን ያህል ይጣጣማል ?

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ