1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ዜጎች ውህደት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ኅዳር 7 2003

እዚህ ጀርመን የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን ከህብረተሰቡ ጋር የማዋሃድ ዓላማ ይዞ የተጀመረው የውህደት መርሀ ግብር ከተጀመረ 5 ዓመታትን አስቆጥሯል ። የቋንቋ የታሪክና የባህል ትምህርት ን ያካተተውን ይህን መርሀ ግብርም በመጪዎቹ 5 ዓመታት አስፋፋቶ ለመቀጠል ታስቧል ።

https://p.dw.com/p/QAZ3
ምስል AP

በጥቅምት ወር መጨረሻ ጀርመን መዲና በርሊን በተካሄደ ዓመታዊ የውህደት ጉባኤ ላይ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፣ እንዳስገነዘቡት መንግስት በዚህ ጊዜ ውስጥ የውህደት ትምሕርት የሚያስፈልገውን እያንዳንዱን የውጭ ዜጋ ማስተማር ይሻል ። በአጠቃላይ ሂደቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ 5 ዓመት ድረስ ፣ የዕድሉ ተጠቃሚ የውጭ ዜጎች ቁጥር ወደ 1.8 ሚሊዮን እንደሚጠጋም ይገምታል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የውጭ ዜጎች ከጀርመን ህብረተሰብ ጋር እንዲዋሀዱ በተያዘው ጥረት በችግሮቹና በመፍትሄዎቹ ላይ ያተኩራል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ