የዐባይ ተፋሰስ አገሮች ትብብር ወይስ ድብቅ ፍጥጫ፣
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2005፤ ሱዳንና ግብፅ፣ በተለይ አሁን የህዝቧ ቁጥር 80 ሚሊዮን መድረሱ የሚነግርላት ግብፅ፤ ከትብብር ይልቅ ወታደራዊ ጡንቻን እንደ አማራጭ ይዛ ከማሰላሰል አለመቦዘኗን አንዳንድ መገናኛ ብዙኀን ይጠቁማሉ። የተፋሰሱን ሃገራት የትብብር አቋም የሚመረምሩ ምን ይላሉ?
ውሃ ህይወት ነው። በተለይ ምድረ በዳ የሆነ አገር ላላቸው ሰዎች፤ የውሃ ሀብት እጅግ ላቅ ያለ ትርጉም ነው የሚሰጠው።ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ግብፅ ናት። በዐባይ ወንዝ ላይ ህልውናዋ የተመሠረተው ግብፅ፤ ለውሃው ከመሠሠቷ የተነሣ፣ ውሃው የሚመንጭባቸው አገሮች በተፈጥሮ ሃብታቸው ያላቸውን የመጠቀም መብት በጭፍኑ ማወቅ እንደማትሻ ተስተውሏል።
ከሞላ ጎደል ሁሉም የተፋሰሱ ሃገራት ውሃውን ፍትኃዊ በሆነ መልኩ ለራሳቸውና በጋራም መጠቀም አግባብነት አለው ብለው ቢያምኑም፤ በተለይ ግብፅና ሱዳን የሚፈለገውን ያህል ሲተባበሩ አይታዩም። አንዳንዴም በምሥጢር ፤ በተለይ ግብፅ የኃይል እርምጃ የመውሰድ፣ ማለት በጦር ኃይል የመጠቀም ዓላማ ያላት መሆኑን አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች መጠቆማቸውን ልብ ይሏል።
የዐባይ ተፋሰስ አገሮችየወደፊት አካሄድ በትብብር ወይስ በፍጥጫ የተመረኮዘ ነው?ባለፉት 38,39 ዓመታት ገደማበውሃና አካባቢ ጥበቃ መሥክ ሥራ ላይ ፤ በመንግሥት መ/ቤትም በግልም የሠሩት፤ ካርቱም ውስጥ፤ ለ 6 ዓመታት ያህል በናይል ተፋሰስ አገሮች፣ የትብብር መድረክ ቢሮ የሠሩትና አሁን፤ በግል በማማከር ተግባር ላይ የተሠማሩት ኢንጂኔር ጌዴዎን አስፋው ፣ እንዲህ ይላሉ።
6 የዐባይ ተፋሰስ አገሮች፤ የትብብሩን ውል የፈረሙ ሲሆን፣ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክም ይህን ታደረጋለች ተብላ በመጠበቅ ላይ ናት። ደቡብ ሱዳንም የብዙኀኑን ፈለግ የመከተል ፍላጎት እንዳላት ነው የሚነገረው። ግብፅና ሱዳን፤ ኢንጂኔር ጌዴዎን ጌታሁን እንደሚሉት፤ የሁኔታዎች ለውጥ መኖሩን በመገንዘብ፤ ከመተባበር ሌላ ተቃራኒውን መንገድ የመከተሉ ሂደት እንደማያዋጣ ሳይገነዘቡ አልቀሩም።
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ