1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ሕዝብ ቁጥር ይጨምራል፤የተመድ

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2001

የተመድ አሁን ያለዉ የሕዝብ ቁጥር በመጪዉ የአዉሮጳዉያኑ 2012ዓ,ም ሰባት ቢሊዮን እንደሚደርስ አስታወቀ። ቁጥሩ በክፍተኛ ደረጃ የሚጨምረዉም በተለይ በእስያና አፍሪቃ በሚገኙ አዳጊ አገራት እንደሚሆን ተገምቷል።

https://p.dw.com/p/HAhM
በታዳጊዉ ዓለም ታዳጊዎች ይበዛሉ
በታዳጊዉ ዓለም ታዳጊዎች ይበዛሉምስል Deutsche Stiftung Weltbevölkerung (DSW)

በተመሳሳይም አሁን ያለዉ ስድስት ነጥብ ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር በ2050ዓ,ም ዘጠኝ ቢሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ድርጅቱ ግምቱን ይፋ አድርጓል። ለባለሙያዎች አሳሳቢዉ ነገር የሕዝብ ቁጥርና የምጣኔ ሃብት እድገት አለመመጣጠን ነዉ። በአዳጊ አገራት ቤተሰቦች የልጆቻቸዉን ቁጥር መመጠን ቢሹም ስልቱ አልተመቻቸም። የበለፀጉት አገራት ደግሞ ሴቶቻቸዉ እንዲወልዱ ያበረታታሉ፤ የሚወልዱ ጥቂት ሆኑ።

SL/NM