1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ባንክና የኢትዮጵያ ልማትፕሮጀክቶች

እሑድ፣ ነሐሴ 5 2005

በማደግ ላይ የሚገኙ ሃገሮች ከተለያዩ መንግስታትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የልማት ርዳታ ያገኛሉ። ኢትዮጵያ አፍሪቃ ዉስጥ ከፍተኛ የልማት ርዳታ ከሚያገኙ ሃገር ግንባር ቀደሟ ናት

https://p.dw.com/p/19NHc
Die Farm von der Größe Luxemburgs des indischen Agrarmultis in der Gambella-Provinz
ምስል DW

ሆኖም ከሚከናወኑ የልማት ተግባራት ጋ በተገናኘ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል በሚል በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዉሞ ፖለቲካ ኃይሎች አቤቱታ ያሰማሉ። ከለጋሽና አበዳሪ አካላት አንዱ የሆነዉ የዓለም ባንክ ይህን አስመልክቶ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ለረዥም ጊዜያት ትኩረት አልሰጠም እየተባለ ቢወቀስም በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን በተለይም ጋምቤላ ዉስጥ ምርመራ እንዲካሄድ የድርጅቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ወስኗል። ጉዳዩን ሲያቀርቡ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ሟጋች ድርጅቶች ርምጃዉ ዘግይቷል ባዮች ናቸዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ