1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ባንክ ዘገባ እና ትችቱ

ሐሙስ፣ ኅዳር 29 2009

ኢትዮጵያ ወጪዋ ከገቢዋ ጋር ባለመመጣጠኑ በምጣኔ ሃብቷ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ የዓለም ባንክ ትናንት አስታወቀ። በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ የተከሰተዉ ድርቅ ችግር ቢፈጥርም የሀገሪቱ የኤኮኖሚ እድገት በመጠኑም ቢሆን መረጋጋት ማሳየቱንም ድርጅቱ ባወጣዉ ዘገባ አመልክቷል።  

https://p.dw.com/p/2TyCi
Addis Abeba Äthiopien Bahn Straßenbahn Haltestelle
ምስል picture-alliance/dpaMarthe van der Wolf

Beri. Washington DC (Critic on WB Ethiopian economic report) - MP3-Stereo

የዓለም ባንክ ለአምስተኛ ጊዜ ባወጣዉ ዘገባዉ አክሎም የባቡር መስመር ግንባታዎች ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ለጎረቤት ሃገራት የማቅረቡ እንቅስቃሴ የሀገሪቱን የዉጭ ንግድ አቅርቦት እንደሚያሻሽልም አመልክቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የሚኖሩ አንድ የመስኩ ጠቢብ ግን ዘገባዉ ጥቂት እዉነታን ብቻ ያገናዘበ ነዉ ሲሉ ይተቻሉ። የባቡር የኤልክትሪክ ኃይል እና የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታዎች በብዙ ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና ብድር መምጣታቸዉንም መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ