1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ተግባር በኢትዮጵያ፣

ሐሙስ፣ የካቲት 7 2005

በዛሬዋ ዩክሬይን በሚገኘው ልሣነ-ምድር ክሬሚያ 3 ዓመት የፈጀው ጦርነት ፤ የተካሄደው አሠቃቂ ጦርነት ባከተመ በ 3ኛው ዓመት ፣ ሎምባርዲያ ፣ ኢጣልያ ውስጥ በምትገኘው ሶልፈሪኖ በተባለችው ንዑስ ከተማ ፣ በኦስትሪያ መንግሥትና በፈረንሳይ ንጉሥ ናፖሊዮን

https://p.dw.com/p/17eG4
ምስል AP

ሣልሳዊ በተደገፈው የሰርዲኒያ መንግሥት መካከል ሰኔ 24 ቀን 1959 በተካሄደ ጦርነት 15,000 ያህል ወታደሮች ባሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን ባጋጣሚ የተገነዘቡት የጀኔቩ ታዋቂ ነጋዴ ፣ እስዊትስዘርላንዳዊው ኦንሪ ዱና፣ ስለአሠቃቂው ጦርነት መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ፣ በ 1863 ቁስለኞችን የሚያክም ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት መሠረቱ። እ ጎ አ ከ 1876 አንስቶ ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የሚል ስያሜ ያገኘ ሲሆን ፣ ድርጅቱ ዘንድሮ 150 ኛ ዓመቱን በማሰብ ላይ ነው። በተለያዩ አገሮች ዓለም አቀፍ የልዑካን ቡድን ያሠማራው ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ምን አከናውኗል ? አሁንስ ምን ዓይነት አገልግሎት በመስጠት ይገኛል?በ 1864፤ በ 12 የአውሮፓ አገሮች፤ ከዚያም በመላው ዓለም ተቀባይነትን አግኝቶ የተስፋፋው ቀይ መስቀል፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ ፤ ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ፤ በጦር ግንባር የቆሰሉ ወታደሮችንና በሠናፍጭ ጋዝ የተጎዱ ሲብሎችን በማከም አገልግሎት ሰጥቷል። ከ 1969

Sudan Rotes Kreuz
ምስል ICRC/P. Yazdi

አንስቶም ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ተግባሩን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ፤ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ ቃል አቀባይ አቶ ዘውዱ አያሌው ስለ ኪሚቴው ዐበይት ተግባራት እንዲህ ገልጸውልናል።በጦር ግንባር ቁስለኞችን ማከም፤ የአካል ጉዳተኞችን መንከባከብ፤ የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ ሌሎች ሰብአዊ እርዳታዎችንም እንደሚያከናውን ፣ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ ቃል አቀባይ አቶ ዘውዱ አያሌው እንዲህ ነው ያብራሩት።

ከኤርትራ ጋር የጦር ምርኮኞች ልውውጥ ተጠናቆ እንደሁ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ሲመልሱ----

በጎ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኘው የ 150 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረው በኢትዮጵያ ፣ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ ፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ አሪያነ ቶምቤት ፣ የማኅበሩ ኮሚቴ ፤ በየትኛውም ቦታ ፣ ወደ ኦጋዴን ጭምር በመንቀሳቀስ ይሠራ እንደሁ ጠይቄአቸው ነበር።

Opfer Landminen Streubomben
ምስል dpa

«ባልደረባዬ በዛ ላሉ ዓመታት ፣ ምን- ምን ዓይነት ሥራ ሥንሠራ እንደቆየን ሳይገልጽልህ አልቀረም። አሁን ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች፣ ምንጊዜም፣ ለምሳሌ፣ በትግራይና የተለያዩ አካባቢዎች፤ተግባራችንን አከናውነናል።

ኦጋዴንን በተመለከተ፤ ልታውቅ የሚገባህ ፣ ለብዙ ዓመታት በቦታው ተገኝተን መሥራታችንን ነው። ሆኖም ወደ ኋላው ላይ የሥራ እንቅሥቃሴአችን ሊገታ ችሏል።

የሆነው ሆነ፣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባለፉት ጥቂት ዓመታት፣ በጣም ጥሩ ገንቢ ውይይት በማካሄድ ላይ የቆየን ስንሆን፤ ወደ ኦጋዴን ተመልሰን እንደምንቀጥል ተስፋ አለን።»

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ